ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመስቀል አደባባይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ይካሄዳል − የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል
#Ethiopia | የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት ካውንስል “መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ነገ እና ከነገ ወዲያ በመስቀል አደባባይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ካውንስሉ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። በመግለጫውም ከ1 ሺህ 600 በላይ አብያተ−ክርስቲያናት ከቢል ግራሃም የወንጌል ማኅበር ጋር በመተባበር፤ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የቄስ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ግራሃም መጋበዛቸው ተጠቁሟል። ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጲያ ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ባላፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸው ተጠቅሷል።

Source: GetuTemesgen









No comments yet.