ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፒፕልስ ከሜሪጆ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ2 ዓመት ሊዘልቅ ፕሮጀክት በመዘርጋት በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ህጽናትና አረጋውያንን ከጎዳና በማንሳት እየተንከባከበና እያስተማረ ሲሆን በተለይ ለታዳጊዎቹ ተማሪዎች ቁሳቁስ ከማቅረብም ባሻገር ሜሪጆይ አስገንብቶ በቅርቡ ለሚያጠናቅቃቸው ሆስፒታል ግብአት የሚሆኑ ዕቃዎችን ከአውሮፓ ለማስመጣት፣ በቁሳቁስና በገንዘብ ለመደጋገፍ፣ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶችን በጋራ ለማሰናዳት መስማማታቸውን ነው ለመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች የገለጡት።
“ሁሉም ልጆች ተሰጥኦና ራእይ አላቸው!” በሚል መርህ የሚንቀሳቀሰው ሆፕ ፎር ኢትዮጵያን ፒፑልስ ድርጅት ፖለቲካዊ ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ማህበር ሲሆን ማህበሩ እ.ኤ.አ. የካቲት 15 ቀን 2021 በጀርመን ሀገር የተመሰረተ ተቋም እና በጀርመን በሚኖሩ ኢትዮጵያዊ አቶ ኢሳያስ ደጀኔ እና የጀርመን ተወላጅ በሆኑት ወልፍጋንግ ትዋርዳዋ አማካኝነት መመስረቱን ነው አቶ ዘውዱ ገዛኸኝ (የድርጅቱ ምክትል ተጠሪ) ነግረውናል።
ማህበሩ በኢትዮጵያ በተለየ መልኩ የልጆችን ራእይና ተሰጥዖ ለማሳካት እና ለመደገፍ እንዲሁም ለተቸገሩ ወገኖች እርዳታ ለማድረስ ድጋፍ እና ማህበራዊ አገልግሎት እንደሚሰጥም ነግረውናል።
ከተመሰረተ 31 ዓመት የሆነው ሜሪጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ተቋሙ በርካታ ልጆችን አስተምሮ ለከፍተኛ ቁምነገር በማድረስ ሀገርና ህዝባቸውን የሚጠቅሙ እንዳደረገ ገልጸው በክልልና በአዲስ አበባ የተለያየ ተግባራትን በማከናወን ላይ ላለው ሜሪ ጆይ በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጲያውያን በገንዘብም በአይነትም በ 0994535353 በመደወል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።



Source: FastMereja









No comments yet.