በእግር ኳስ ኮኮቡ ማራዶና ሞት የተከሰሱት የህክምና ሞያተኞች የፍርድ ሂደት ተጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | እኤአ ኖቬምበር 2020 ህይወቱ ያለፈው አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ጥበበኛ ማራዶና፤ አደገኛና ርህራሄ የለሽ ህክምና ሰጥተዋል የተባሉ ሰባት የጤና ባለሙያዎች ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ከምንግዜም የእግርኳስ ምርጦች መካከል አንዱ የሆነው ዲያጎ ማራዶና ከሞት አራት ዓመታት የተቆጠረ ቢሆንም በኮኮቡ የመጨረሻ ቀናት የሙያ ስነምግባርና ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ሞያተኞች ለፍርድ ቀርበዋል።

በፍርድ ሂደቱ ላይ የማራዶና ቤተሰቦችና የግል ዶክተሮች ጨምሮ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች ፍርድ ቤት ተገኝተው የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዛሬ አርብ ማለዳ በወጡ መረጃዎች መሰረትም የምስክሮች ቃል የመሰማት ሂደቱ ከቀጣይ ማክሰኞ ጀምሮ ለአራት ወራት ገደማ ይቀጥሏል ተብሏል።

ሰባቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከስምንት እስከ 25 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል። በ60 ዓመቱ እኤአ ኖቬምበር 25 ቀን 2020 ላይ ህይወቱ ያለፈው ማራዶና የገጠመው የደም መርጋት ችግር ለማስወገድ የተሳካ ቀዶ ህክምና አድርጎ በጥሩ እያገገመ ነበር። ነገር ግን ይህ ነገሮች በቶሎ ተቀያይረው ማራዶና በቦነስ አይረስ በተከራየው ወኖርያ ቤቱ አልጋ ላይ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

ከህልፈቱ በኃላ ይፋ የተደረገው የህክምና መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ማራዶና በልብ ድካም ህይወቱ አልፏል። በሰዓቱም በማራዶና ቤት የምሽቱ ተረኛ ነርስ የነበረችው ባለሞያ ምንም እንኳ በእንቅልፍ ላይ ሆኖ የልብ ድካም ምልክቶች እንዳሳየ ብትመለከትም እንዳትቀሰቅሰው መመርያ ስለተሰጣት በዝምታ ለማለፍ እንደተገደደች ገልፃለች። በዚህም በወቅቱ የማራዶናን የጤና ሁኔታ ሲከታተሉ የነበሩ ሰባት ሙያተኞች ተከሰው ፍርድ ቤት ለመቅረብ ተገደዋል።

#BisratFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1