#FastMereja I በላይ አብ ሞተርስ ከቻይናው ዶንግፌንግ የመኪና አምራች ኩባንያ የተረከባቸውን 50 የኤሌክትሪክ መኪኖች ዛሬ የካቲት 28/2017 ዓም ለተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር አባላት አስረከበ።
ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዛሬ ከበላይዓብ ሞተርስ የተረከባቸውን መኪኖች 25 በመቶ ለቆጠቡ አባላቶቹ ነው ዛሬ ያስረከበው። ተሽከርካሪውን የተረከቡት ባለንብረቶች ከ5 እስከ 10 አመት ያለባቸውን ቀሪ ክፍያ በሂደት ከፍለው ያጠናቅቃሉ ተብሏል።
ከሰባት አመት በፊት የተመሰረተው ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር በ24 መስራት አባላት በ24 ሺህ ብር የተቋቋመ ሲሆን ዛሬ 250 ሚሊዮን በላይ ካፒታል እና 8300 በላይ አባላት እንዳለው ተነግሯል።
#ቢዝነስ



Source: FastMereja









No comments yet.