ኢትዮጵያ ከጦር መሳሪያ ሽያጭ ከወዲሁ ከ30 ሚሊየን ዶላር በላይ አገኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናትናው እለት አምቦ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የሆሚቾ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኢንደስትሪን በጎበኙበት ወቅት ፋብሪካው ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ እና ተተኳሾች እያመረተ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

“ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፡፡ በታሪኳና በሃብቷ ልክ እራሷን ጠብቃ ለልጆቿ መሸጋገር መቻሏን ማረጋገጥ ያስፈልጋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ አቅራቢያ ላይ የሚገኘውን የሆሚቾ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ኢንደስትሪን በጎበኙበት ወቅት አሁን እውን ሆኗን ያሉት የጦር ማሳሪያ ፋብሪካው ምርት ማምረት ከዚህ በፊት በብዙ ተሞክሮ ያልተሳካው ነገር ነበር፡፡

የኢንደስትሪውን አስፈላጊነት ሲያረዱም፤ “እንደዚህ አይነት ስትራቴጂክ አቅሞች ኢትዮጵያ ካልገነባች በሆነ ጊዜ ማንም መጥቶ ጥቃት ልፈጽምባት ይችላል የሚል ግምገማ ነበረን፡፡ 2014 ዓ.ም. ጥይት እንገዛ ነበር፡፡ 2015 ዓ.ም. ነው ፋብሪካውን መትከል የጀመርነው” ሲሉም ፋብሪካውን ከሌሎች ከፍተኛ የአገሪቱ የጦር አመራሮች እና ባለስልጣናት ጋር በጎበት ወቅት ተናግረዋል






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1