የእርዳታ ተማጽኖ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | “ማሩ ሞላ ስንደቄ እባላለሁ ትውልድና እድገቴ ባህርዳር ከተማ ነው በባዮሎጅ የትምህርት መስክ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ድግሬ ተመርቂያለሁ።

በተለያዩ የመንግስት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በማስተማር ና የተለያዩ ሀላፊነቶች የስራው ሲሆን ከ2003 አ ም ጀምሮ ደብረታቦር በሚገኘው በጌምድር መምህራን ኮሌጅ መምህር ሁኘ ስሰራ ቆይቻለሁ።

ከጥር 2010 ጀምሮ በድንገት ህመም ሲስማኝና ስመረመር የሁለቱ ኩላሊቶቸ መድከሙንና ስራ ማቆሙን በተለያዩ ዶክተሮች ተነገረኝ።ወድያውኑ ስራ አቆምኩ ሙሉ ታማሚ በሽተኛ ሆንኩ። ክስተቱ ልብ ሰባሪና ተስፋ አስቆራጭ ነበር።በሽታው እያደከመኝ ሲመጣ ና መንቀሳቀስ ሲሳነኝ የኩላሊት እጥበት(dialyasis) ጀመርኩኝ ።

በአሁኑ ሰአት በሳምንት ሁለት ጊዜ ዳይላያሲስ አደርጋለሁ።

በፈለገህይወት ሆስፒታል ለአንድ ዳይላያሲስ 6,000 ብር በሳምንት ሁለት ጊዜ 12, 000 በወር እስከ 50, 000 በግል እየከፈልኩ እታከማለው።ከኮረና ጀምሮ አሁን ድረስ ባለው አገራዊ ችግር የህክምነው ዋጋ በየአመቱ አጥፍ መጨመርና የመዳህኒትና ግባእት እጥረት የእኔ አይነት ታማሚወችን ህይወት ፈታኝ አድርጎታል ።

የዳይላያሲስ ህክምና በጣም ውድ ከመሆኑ የተነሳ ያለኝን ንብረት በመሸጥና በእዳ በማስያዝ ህክምናውን ለ ሰባት አመታት ስከታተል ቆይቻለሁ።በዚህ ላይ ባለትዳር ና የሁለት ህጻናት ልጆች አባት ነኝ።

በሽታው የኢኮኖሚ አቅምን ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ የሰውነት አቅምን ስለሚያደክም ለተለያዩ ተጓዳኝ በሽታወች ስለሚያጋልጥ አብዛኛው ታማሚወች በህይወት የሉም።እኔ በፈጣሪ ሀይል በህይወት አለው።ከዚህ አስከፊ ችግር ለመውጣት የንቅለ ተከላ ህክምና ለማድረ አስቢያለው።

በመሆኑም የባህርዳር ፈለገህይወት ሆስፒታል እንዲሁም የጎንደር ዩኒሸርስቲ ሆስፒታል ቦርድ ንቅለ ተከላ ህክምና እንዳደርግ ቢወስንም ህክምናዉን በውጭ ሀገራት ለማድረግ ከ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተብያለሁ ።

ለረጅም አመታት በከፍተኛ የህክምና ወጭ ስለቆየው ይህንን ከፍተኛ ወጭ ከፍሎ መታከም አልችልሞ።

ስለሆነም በእናንተ በኩል ለህክምና ወጭ የማውለው ገንዘብ እንድታሰባስቡልኝ በእግዚያብሄር ስም እየጠየኩ ለዚሁ ተግባር የተቋቋመው የኮሚቴ የባንክ አካውንት
1000677642018
(Getachew Adugna & mesfin Demilew & Solomon Chanie) መሆኑን እገልጻለሁ።

+251 92 452 3606
ታማሚ ማሩ ሞላ)
አስታማሚ መስረት ሽፈራው
091 871 4398





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2