#Ethiopia | መጥፎ ፀባዮች አሉብኝ፤ ዘረኝነት ግን በፍፁም የእኔ ባህርይ አይደለም ሲሉ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ተናገሩ።
አሰልጣኙ፤ እኔ ማን እንደሆንኩ ሁሉም ያውቃል። መጥፎ ባህሪያት አሉብኝ ብዙ ሰው ያውቃል። ነገር ግን ዘረኝነት ከመጥፎ ባህሪዎቼ አንዱ አይደለም። ዘረኝነት በጣም የምጠላው ነገር ነው ብለዋል።
ከሳሾቼ የታሪክ ዳራዬን ስለማያውቁ እኔን ለማጥቃት ብልህ አልነበሩም ያሉት ሞሪንሆ፤ ከአፍሪካ ሰዎች ጋር ስለ አለኝ ግንኙነት መረጃ የላቸውም ብለዋል።
አሰልጣኝ ሞሪንሆ በጋላታሳራይ የቀረበባቸውን የዘረኝነት ክስ በተመለከተ ከእስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ክሱ መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግረው፤ የጋላታሳራይ ክለብ ከአፍሪካውያን ጋር ያለኝን ግንኙነት አላወቀውም ብለዋል።
ሞሪንሆ ባለፈው ሰኞ 0 ለ 0 ከተለያዩት ጨዋታዎች በኋላ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የጋላታሳራይ ቤንች የ19 ዓመቱ የመሀል ተከላካይ ዩሱፍ አኪሴክ በጨዋታው መጀመሪያ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጣ ለማድረግ “እንደ ዝንጀሮ እየዘለሉ ነው” ሲሉ ከሰዋል።
ሰው ነኝ እንደሰው መጥፎ ፀበዮች አሉብኝ ያሉት ሞሪንሆ፤ ዘረኝነት ግን በፍፁም የእኔ ባህርይ አይደለም ብለዋል።
የሚያሰለጥኑት ክለብ የፌኔርበቼ ደጋፊዎች ለጆዜ ያላቸውን ድጋፍ ባነር ይዘው በመግባት አሳይተዋል።
በቅርቡ የጋላታሳራይ ደጋፊዎችን በዘረኝነት ተሳድበዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
#ጋዜጣ_ፕላስ
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen








No comments yet.