#Ethiopia | የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ የተፈፀመውን የስርቆት ወንጀል በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታዉቋል።
ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25.7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር መዘረፉ የክልሉን መንግስት አሳዝኗል ብሏል።
በዚህ ክስተት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንዳሉት፣ በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት በገቢረሱ ዞን በተፈፀመው ስርቆት ከ717 ሺህ ዶላር በላይ እና ከ25.3 ሚሊየን ብር በላይ ኪሳራ ተመዝግቧል።
የኤሌክትሪክ ኃይሉ የሰሜን ምስራቅ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው ሪጅኑ ሶስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ከ436 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የማስተላለፊያ መስመሮችን እንደሚያስተዳድር ገልፀዋል።
ተቋሙ ለህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ ለማዳረስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችና የኮንዳክተር ሽቦ ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል ማነቆ እንደሆነ አስረድተዋል።
የዞንና የወረዳ እንዲሁም የፀጥታ ዘርፍ አካላት በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው በኃይል መሰረተ ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈፀም በር ከፍቷል ተብሏል።
#capital
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.