የመጋቢት ወር የደም ልገሳ መረኃግብር በይፋ ተጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

በመጋቢት ወር ከሚከናወኑ ስራዎች ውስጥ ወሩን በተለያዩ የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችና በበጎ ፍቃድ የደም ማሰባሰብ ንቅናቄዎችን ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ የደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ሃገር አቀፍ የንቅናቄ ዘመቻ በአዲስ አበባ 15ሺ ዩኒት ደም፣በመላ ሃገሪቱ ደግሞ 55 ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል የተባለ ሲሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው መጋቢት የበጎ ፍቃድ የደም ልገሣ ወር አላማ በዋነኝነት በ2017 ዓም እንደ ሃገር 55ሺ ዩኒት ደም ለመስብስብ መታቀዱ ተገልጿል።

የማህበረሰቡን የደም ልገሳን ባህሉ በማድረግ በየሶስት ወሩ በመደበኛነት እንድለግስ ለማበረታታት መጋቢት ወር በየእመቱ “የደም ልገሳ ወር መሆኑ ታዉቆ በልዩ ትኩረት የደም ማሰባሰብ ስራ ለመስራት እና ደምና የደም ተዋጽኦ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ያለምንም የእጥረት ሥጋት ተደራሽ ለማድረግ፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት መተባበር እንዳለብን ተጠቁሟል።

በመሆኑም ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በመላ ሃገሪትቱ መጋቢት ወር የደም ልገሳ ወር ተብሎ በይፋ የንቅናቄ ስራው የተጀመረ መሆኑን ተገልጾ ውድ ደጋግና ባለቅን ልብ ኢትዮጵያዊያን ደም ድንበር የለሽ ከሰው ልጅ ብቻ የሚገኝ የሰው ልጅ ህይወትን የምንታደግበት በነፃ በመለገስ የወገኖቻችን ህይወት የምናተርፍበት በገንዘብ የማይተመን ውድ የህይወት ስጦታ መሆኑን ተረድታችሁ በሚተካው ደም የማይተካውን ህይወት ለማትረፍ በጋራ
መረባረብ ይገባል ተብሏል።

ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ እና ኪሎ ከ45 ኪግ በላይ የሆናችሁ በጎ ፍቃድ ደም ለጋሾች በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ 54ቱም የደም ባንክ ቅርንጫፎች ወይም ለደም ልገሳ ተብለው በሚዘጋጁ ተንቀሳቃሽ ጣቢያዎች “ደማችን ለእናቶች ፤ ደማችን ለልጆች ደማችን የደም ህክምና ለሚያስፍልጋቸው ታካሚዎች ለሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ” እንድንለግስ
ጥሪ ቀርቧል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: