የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት፣።
በትናንትናው ዕለት በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ የተጻፈ ደብዳቤ፣ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ኃይለ ለጊዜው መታገዳቸውን ያስረዳል።
መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የተጻፈው ይህ የዕግድ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ሦስቱ ከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች የታገዱት “ከመንግሥት ውሳኔ ውጪ መላ ሕዝባችንንና ወጣቱን ወደ ግርግር፤ የፀጥታ ኃይላችንን ወደ እርስ በእርስ ግጭት ብሎም ሕዝባችንን ወደማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ አልቆመም” በሚል ነው።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሦስቱ ከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች ላይ የዕግድ ውሳኔውን ያስተላለፈው በዚህ ምክንያት መሆኑም ተጠቅሰዋል።
ይህ ሁኔታ “ሥርዓት ባለው አካሄድ መግባባት እስኪደርስበት ድረስ”፤ ከፍተኛ የጦር መኮንኖቹ “ከሠራዊት ግንባር የማዘዝ ኃላፊነታቸው ላልተወሰነ ጊዜ” የታገዱ መሆኑን አቶ ጌታቸው በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል።
ለእነዚህ ከሠራዊቱ አዛዥነታቸው ላልተወሰነ ጊዜ የታገዱት አመራሮች በየግላቸው የተጻፈው ደብዳቤ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኃላፊ እና የትግራይ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲያውቁት ግልባጭ ተደርጓል።
እነዚህ ሦስቱን የግንባሩ አዛዦችን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የሠራዊቱ አዛዦች ድጋፋቸውን በደብረፂዮን ገብረሚካኤል ለሚመራው የህወሓት ቡድን ሲገልጹ እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለውጥ እንዲደረግ ሲጠይቁ ነበር ተብሏል።
የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች በዚሁ የአቋም መግለጫቸው ላይ በዶ/ር ደብረጽዮን ለሚመራው የህወሓት ጎራ ዕውቅና መስጠታቸው ይታወሳል።
ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል “በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል” በማለት ባስጠነቀቁበት ጽሑፍ ላይ፣ በትግራይ አመራሮች መካከል ያለውን ክፍፍል በመጥቀስ “ከቀደመና ከአሁንም ወንጀላቸው ተጠያቂነት ለማምለጥ ከኤርትራ ጋር መወገን የሚመርጡ የትግራይ ልጆች አሉ” ሲሉም ተናግረዋል።
በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል በቀጠለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ጦርነት ሊያመሩ እንደሚችሉ መሰማት የተጀመረው።
ጄኔራል ፃድቃንም ይህንን የህወሓት ክፍፍል በመጥቀስ “ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በመወገን ዐቢይ አሕመድን ከሥልጣን ለመገልበጥ” የሚፈልጉ መኖራቸውን ጠቁመዋል።
Source: Yeneta Tube









No comments yet.