የአልሸባብ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ሶማሊያ በሚገኝ ሆቴል ባደረሱት ጥቃት የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡የአልሻባብ ታጣቂዎች በማዕከላ…

- Advertisement -
Sidebar AD
⚡️የአልሸባብ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ሶማሊያ በሚገኝ ሆቴል ባደረሱት ጥቃት የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የአልሻባብ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ሶማሊያ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ ከበባ በማድረግ በሆቴሉ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
ከጥቃቱ ሰአታት በኋላ የመንግስት ሃይሎች በቦታው ደርሰው ከታጣቂዎቹ ጋር ተኩስ መክፈታቸዉ ተገልጿል፡፡
አልሸባብ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዶ፤ ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉን አስታውቋል።
ጥቃቱ በደረሰበት ሆቴል የአልሸባብን ጥቃት እንዴት መመከት ይቻላል በሚል ስብሰባ ሲካሄድ ነበር፡፡
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው አልሻባብ አሁንም በሶማሊያ የራሱን መንግስት ለመመስረት በማለም የተለያዩ ጥቃቶችን መፈጸሙን እንደቀጠለ ነዉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1