#Ethiopia | ውድነሽ ወርቁ ትባላለች። የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪ ነች። የአንድ ልጅ እናት ። ገና በወጣትነቷ የአጥንትና የነርቭ ችግር አጋጥሟት የአልጋ ቁራኛ ከሆነች አምስት አመት ሞልቷታል።
ቤተሰቧ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር በመሆኑ የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። አሁን ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ አትችልም። ለአምስት አመት የተኛችበት አካሏ ቆሳስሏል።
ከባድ መከራ ውስጥ ነች። እንርዳት።
መላ ኢትዮጵያዊያን ህይወቷን እንዲታደጉት ጠይቃለች። እናቷም አሁን ጉልበታቸው ደክሟል። ከወትሮውም አረቂ በማውጣት የሚተዳደሩት እናቷ በደከመ አቅማቸው የልጃቸውን መውደቅ እያዩ ሁልጊዜ ያነባሉ።
ልጃቸውን የኢትዮጲያ ህዝብ እንዲያድንላቸው በእንባ ጠይቀዋል።
አካውንት ቁጥር 1000235378241
ስ.ቁ 0974730085
በጋዜጠኛ ዘላለም ገበየሁ


Source: GetuTemesgen









No comments yet.