ጌታቸው ረዳ በሶስቱ ጄነራሎቹ ላይ የጣሉትን እገዳ አልቀበልም፣ ተፈጻሚነትም አይኖረውም

- Advertisement -
Sidebar AD

ሲል ሕወሓት መግለጫ ሰጠ።

“ህወሓት የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ብሄራዊ ክህደት የፈጸሙ እና እየሰሩ ነው ያላቸውን “አመራሮችን በማባረር በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ውክልና ባነሳም”፣ “ቀድሞው ፕሬዝዳንት” ሲል የጠራቸውን አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት “ከህግና ስርዓት ውጪ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል።” ሲል መግለጫውን ጀምሯል።

“የህዝባችንን አንድነት በማደፍረስ የትግራይን ሁለንተናዊ አቅም በማዳከም ብሄራዊ ክህደት እየፈፀመ ያለው የቀድሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ለመፋለም የተደራጀውን የትግራይ ሰራዊት ለመበተን ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።” በማለት የቀጠለው የሕወሓት መግለጫ “የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣናቸው እና ከኃላፊነታቸው ውጪ የትግራይ ጦር ግንባር አመራሮችን አግደዋል።” ሲል ክስ አቅርቧል።

“ይህ ዕገዳ መሠረተ ቢስ እና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ቢሆንም ህዝባዊ ትግሉን ከህግ እና ከስርዓት ውጭ ለማድረግ ቡድኑ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ያሳያል።” በማለት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ኮንኗል።

“ይህ የሰራዊታችን ሰንሰለት መቋረጥ የለበትም። ድርጊቱ ለአደጋ ተጋላጭነታችንን የሚጨምር፣ የትግራይን ህዝብ ሉዓላዊነትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሌላ ክህደት ነው።” የሚለው የሕወሓት መግለጫ ለታጋዮቹ እና በየደረጃው ላሉ የሠራዊቱ አባላት እንዲሁም የፓርቲው አባላት “ይህ በሰራዊቱ አመራሮች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ህገወጥ እና ተፈጻሚነት የሌለው መሆኑን እንድትገነዘቡት” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

“ተንኮለኛ” ሲል የጌታቸው ረዳን ቡድን የፈረጀው ሕወሓት “የህዝባችንን ጥቅም ለመጥለፍ እና አቅማችንን ለማደፍረስ እየሞከረ በመሆኑ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል” ሲል ለታጋዮቹ፣ ለሰራዊቱ አባላት እና ለፓርቲ አባሎቹ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: