ከጅቡቲ አዲስ አበባ ጭነቶችን የሚያመላልሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ የሚጠየቁት የኮቴ ክፍያ ስራቸውን እንዳከበደባቸው ቅሬታቸውን ለሀገሬ ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
አሽከርካሪዎቹ ከጅቡቲ አዲስ አበባ እስከሚደርሱ ድረስ በሚያቋርጧቸው የተለያዩ ክልል ከተሞች እስከ ስድስት ሺህ ብር ድረስ እንደሚጠየቁ ተናግረዋል፡፡
ከጂቡቲ አዲስ አበባ ባለው መንገድ ላይ በተለያዩ ቦታዎች የኮቴ ክፍያዎችን እንደሚጠየቁ የተናገሩት አሽከርካሪዎቹ፤ አይሻ ፣ ድሬዳዋ ፣ ካራሚሌ ፣ ቆቦ፣ ቦረዳ፣ ጭሮ ፣ ደበሶ እና ሞጆ ከተሞች በቋሚነት የኮቴ ክፍያ ከሚከፈልባቸው ቦታዎች መካከል ናቸው ሲሉ አክለዋል።
የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተሸከርካሪዎቹ የሚያጓጉዙት የግንባታ እቃዎች፣ መድሀኒት፣ አልባሳት፣ ምግብ፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ለኢኮኖሚው ትልቅ አበርክቶ ያላቸውን ግብአቶች እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
አሽከርካሪዎቹ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን ለተጠቃሚው ለማድረስ በሚያደርጉት ጥረት በየከተሞቹ የኮቴ ክፍያ መጠየቃቸው ተገቢ አለመሆኑን ለሚመለከታቸው የገቢዎች እንዲሁም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር ሀላፊዎች አሳውቀን ችግሩ እንዲቀረፍ ተቋማቱ ለክልሎቹ ደብዳቤ ቢጽፉም ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል ሲል ማህበሩ ገልጿል።
@seledadotio
@seledadotio









No comments yet.