ካሳቫ የተባለው የስራስር  ዱቄት በእንጀራ ላይ ተጨምሮ  እንዲሸጥ  ተፈቀደ።  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት…

- Advertisement -
Sidebar AD
👀ካሳቫ የተባለው የስራስር  ዱቄት በእንጀራ ላይ ተጨምሮ  እንዲሸጥ  ተፈቀደ። 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለሥልጣን ካሳቫ የተባለው ሥር በእንጀራ መልክ እንዲቀርብ መፈቀዱን አስታውቋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ እስጢፋኖስ  ጌታቸው  ካሳቫ የተባለው ሥር  ከምግብ ምድብ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ከእንጀራ ምርት ጋር ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዲቀርብም  በደረጃዎች ሲፈቀድ እኛ ደግሞ የመቆጣጠር ስራውን እንሰራለን ብለዋል።
ይህንን ተገን በማድረግ ሌላ ባዕድ ነገር እንዳይቀላቀል የቁጥጥር ሥራ ይሠራል ብለዋል።
አሁን ላይ ምርቱ ከክልሎች በመምጣት  አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በስፋት እንደሚገኝም ተነስቷል፡፡
የካሳቫ ተክል ከፍተኛ የካርቦሀይድሬት መጠን ያለው ሲሆን በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ምግብ መሆኑንንም በጥናት ማረጋገጣቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።
ካሳቫ የስኳር በሽታን፣የልብ በሽታን እንዲሁም የህዋስ እርጅናን/cell aging/ እንደሚከላከል ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።
ካሳቫ የስራስር አይነት ሲሆን፤ በተለይ በደቡብ የሀገሪቱ ከፍል  በወላይታ እንዲሁም በጋሞ ዞን ምርቱ በብዛት  እንደሚኝም የባለስልጣኑ ዋና ሃላፊ ጨምረው ገልጸዋል።
@seledadptio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1