#Ethiopia | ድርጊቱ የተፈፀመዉ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደደር ወረዳ ዉስጥ ሲሆን አራት ግለሰቦች በ12 ሴት ህፃናት ላይ ግርዛት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።
የደደር ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት መግለጫ እንደሚያሳየዉ አንደኛ ተከሳሽ ሶፊያ መሀመድ ፣ሁለተኛ ተከሳሾች ኢሊሊ አብዲ እና ናህሊ አብዲ የተባሉ እህትማማቾች እና ሶስተኛ ተከሳሽ ኬዲያ ኢብራሂም የተባሉት ግለሰቦች በተለያዩ ቀናት በ12 ሴት ህፃናት ላይ የግርዛት ድርጊት ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል ።
አንደኛ ተከሳሽ የሆነችዉ ሶፊያ ጳግሜ 1ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በደደር ወረዳ ቢዮ ነጋ ቀበሌ ዉስጥ 6 ህፃናት ላይ የግርዛት ድርጊት ስትፈፅም ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዉላለች ። ሁለተኛ ተከሳሽ እህትማማቾች መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም በ5 ሴቶች ላይ ይህንኑ ድርጊት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊዉሉ ችለዋል ።
ሶስተኛዋ ተከሳሽ በተመሳሳይ መልኩ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በ6 አመት ሴት ልጅ ላይ የግርዛት ድርጊት ልትፈፅም ስትል ለፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ ግርዛቱን ሳታከናዉን በቁጥጥር ስር ዉላለች ። ፖሊስ ከደደር ወረዳ አቃቤ ህግ እና የሴቶችና ህፃናት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት የድርጊቱን ፈፃሚዎች ተከታትሎ በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ መዝገቡን በህክምና ማስረጃ አጠናቅሮ ለአቃቤ ህግ ልኳል።
አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ ቁጥር 565 በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶችን በመገረዝ ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል ። ክሱን የተመለከተዉ የደደር ወረዳ ፍርድ ቤት አራቱ ተከሳሾች በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አማካኝነት የሴት ልጅ ማህፀን ላይ ጉዳት ማድረሳቸው በበቂ ማስረጃ አረጋግጧል።
በዚህም የተነሳ አንደኛ ተከሳሽ በ1 አመት ከ6 ወር እስራትና በ1000 ሺህ ብር መቀጮ እንድትቀጣ ሲወሰን ሁለተኛ ተከሳሽ እህትማማቾች በ1 አመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ። ሶስተኛዋ ተከሳሽም በ6ወር እስራት እንድትቀጣ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የደደር ወረዳ ፍርድቤት ዉሳኔ ማስተላለፉን ብስራት ራዲዮ ከደደር ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።
#BisratFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.