#Ethiopia | የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ገልጿል።
በጥቂት አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
– በደቡብ፤
– በደቡብ ምዕራብ፣
– በመካከለኛዉ፣
– በሰሜን ምስራቅ፣
– በምስራቅና በስምጥ ሽለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡
የበልግ አብቃይ አከባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ።
በዚህ ወር በመደበኛነት ትኩረት ከሚሹ የአየር ሁኔታ ክስተቶች መካከል ቀን ላይ የሚኖረው የሙቀት መጠንና ሌሊት ላይ የሚታየው ወበቅ አንዱ ነው።
በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀት ጋር በተያያዘ ፦
° በጋምቤላ፣
° በአፋር፣
° በሶማሌ፣
° በቤንሻንጉል ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እሰከ ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ.
በደቡብ፤ በመካከለኛና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ በልግ አብቃይ አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት የአፈር ውስጥ የውኃ መጠንን ስለሚያሻሻል የሰብሎች የማሳ ዝግጅት ለማከናውን፣ ለቋሚ ተክሎች፣ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥሩ እድል ይኖረዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ለመዝራት የዘገዩ አካባቢዎች የሚጠበቀውን እርጥበት ለመጠቀም በቂ ዘር ለመዘራት የሚያሰቸል ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ያስፈልጋል።
#EPA
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.