በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ዓይነ ስውርነት በግላኮማ የሚመጣው ቀዳሚው መሆኑ ተነገረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ግላኮማ ሲከሰት ለረጅም ጊዜ ምልክት ለማሳየቱ ብዙዎችን ላይነ ስውርነት እየዳረገ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ዓለም አቀፍ የግላኮማ ሳምንት በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየታሰበ ነው፡፡

በግላኮማ ምክንያት የሚደርሰውን የዓይን ብርሃን ማጣት ለመከላከልም የዓይን ግፊትን በየጊዜው መከታተል እና ምርመራ ማድረግ ይገባል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በቅርብ የተሰራ ጥናት ባይኖርም ከ 19 ዓመት በፊት በነበረው መረጃ በሌሎችም ምክንያቶች የሚፈጠር ዓይነት ስውርነት ውስጥ በግላኮማ የሚከሰተው ቀዳሚ መሆኑን የነገሩን የዓይን ሀኪም እና የግላኮማ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ናሆም አያሌው ናቸው፡፡

አሁን ባለው መረጃ በአለም ደረጃ 80 ሚሊዮን የሚያክል ህዝብ ወይም ሰው በግላኮማ ተጠቂ እንደሆነ ያሳያል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ላይ ግላኮማ በስፋት እንደሚታይ የሚናገሩት ዶክተር ናሆም ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 10 ሺህ ያህሉ በግላኮማ እንደሚያዙ ጥናት ያሳያል ይላሉ፡፡

በተለይ ደግሞ በታዳጊ አገሮች ደሀ በሆኑ ሀገሮች በቀላሉ የህክምና አገልግሎት ሊገኝ የማይችልበት ሃገሮች ላይ በጣም ተስፋፍቶ እንደሚኖር ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ግላኮማ ለረጅም ዓመታት ቢከሰትም ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ በመሆኑ ብዙዎችን ለአይነ ስውርነት እየዳረገ በመሆኑ ሳምንቱ በዚህ ላይ የሚሰራበት ነው ተብሏል፡፡

ማንኛውም ሰው በተለይ ደግሞ እድሜያቸው ከአርባ ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ወደ ዓይን ህክምና ማዕከል በመምጣት እይታቸውን ወይም የዓይን ግፊቱን በመለካት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በግላኮማ ምክንያት የሚመጣውን የዓይን ብርሃን ማጣት በህክምና መመለስ የማይቻል በመሆኑም ቅድመ ምርመራው ላይ መበርታት ያስፈልጋል ተብሏል አንድ ሰው ግፊቱ እየጨመረ ሄዶ የዓይን ብርሃኑን ለማጣት እስከ 15 ዓመት ድረስ እንደሚችልና በተለይ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
#shegerFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: