በኢትዮጵያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የኒውዚላንድ፣ የጃፓን፣ የኖርዌይ፣ የቤልጂየም፣ የቡልጋሪያ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የዴንማርክ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቬንያ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ህብረት ልኡክ ።

በዚህም መግለጫቸው ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ለውጦችን / ሁኔታዎችን እና እየተባባሰ ያለውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

” እ.ኤ.አ. ህዳር 2022 ለተፈጸመው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ ደግመን አጽንኦት እንሰጣለን ” ብለዋል።

ይህ ስምምነት የመሳሪያ ድምጽ ጸጥ እንዳደረገም አመልክተዋል።

በፍጹም ወደ ሁከት ፣ ግጭት ፣ ጦርነት መመለስ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተባብሰው አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ውጥረቱን በማርገብ ስምምነቱን እንዲጠብቁ አጥብቀው አሳስበዋል።

ማንኛውም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ትናንት ጌታቸው ረዳ አምባሳደሮችን በማግኘት ስለ ወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ማስረዳቱ የሚታወስ ነው።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: