#Ethiopia | የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው። ውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)ና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እየተመራ ይገኛል።
በመድረኩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፤ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል።በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ የሰጠውን መመሪያ አለመቀበሉን አስረድተዋል።
የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ መንግስት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እየተከታተለ ነው ብለዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል፡፡
በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕለት ተለት ተግባራት ላይ እክል እየፈጠረ መምጣቱን አስረድተዋል።
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና የፌደራል መንግሥት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል –
#nbc
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et

Source: GetuTemesgen









No comments yet.