#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተባባሰ ባለው የንግድ ጦርነት ከአውሮፓ ህብረት ወደ አሜሪካ በሚመጣ ማንኛውም አልኮሆል ምርት ላይ 200 በመቶኛ ቀረጥ እንደሚጣል ዝተዋል። ትራምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሁሉም የብረት እና የአሉሚኒየም ምርቶች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ለመበቀል የአውሮፓ ህብረት የምበወሰደው እርምጃ 50 በመቶ ታክስ ለመጣል ወስኗል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት የአውሮፓ ህብረት በአሜሪካ ዊስኪ ላይ የጣለውን “አስነዋሪ” ቀረጥ በአስቸኳይ እንዲያነሳ በመጠየቅ ህብረቱን “ጠላት እና ተሳዳቢ” ነው ፤ እንዲሁም “ከዩናይትድ ስቴትስ ለመጠቀም ብቻ የተመሰረተ” ሲሉ ጠርተውታል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይየምስክር ነ ስለ ሁኔታው ለመወያየት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል “የምክክር መድረክ እየተዘጋጀ ነው” ብለዋል ።የንግድ ኮሚሽነሩ ማሮሽ ሼፌኮቪች ከትራምፕ የቅርብ ጊዜ ስጋት በኋላ “ከአሜሪካ አቻዎቻችን ጋር ተገናኝተናል” ሲሉ አረጋግጠዋል። የፋይናንሺያል ገበያዎችን ያናወጠ እና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በበርካታ የዓለም ሀገራት በኢኮኖሚው እና በተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኘው የንግድ ጦርነት ሌላ መባባስን አሳይቷል። የአውሮፓ የወይን ኢንዱስትሪን የሚወክለው ኮሚቴ ዩሮፔን ዴስ ኢንተርፕራይዝ ቪንስ እንዳለው አውሮፓ በየዓመቱ ከ4.89 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የወይን ምርት ወደ አሜሪካ ትልካለች ብሏል።
የቡድኑ ዋና ጸሃፊ ኢግናስዮ ሳንቼዝ ሬካርቴ ትራምፕ ዛቻዎቻቸውን ተግባራዊ ካደረጉ ገበያውን ያወድማሉ፤ ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከስራ እንዲፈናቀሉ ያስገድዳል ሲሉ ተደምጠዋል።ይህን ሁሉ የወይን ምርት ለመሸጥ ሌላ አማራጭ የለም፤›› በማለት ሁለቱ ወገኖች ‹‹ወይንን ከዚህ የንግድ ጦርነት እንዲያድኑ›› ተማጽነዋል።የሰሞኑ ግጭት የተከሰተው አዲስ የአሜሪካ ታሪፍ በብረት እና በአሉሚኒየም ላይ እሮብ እለት ተግባራዊ ከሆነ በኃላ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን ብረቶች 25 በመቶ ቀረጥ በመጣሉ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ሲል አውሮፓ ህብረት እና ካናዳ ጨምሮ ከአንዳንድ ሀገራት ትሰጥ የነበረው ቀረጥ ነፃ መደረጉ ቆሟል።
የአሜሪካ ታላላቅ የንግድ አጋሮች የሆኑት ካናዳ እና አውሮፓ አዲሶቹን ታክሶች ፍትሃዊ አይደሉም በማለት በተለያዩ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የአፀፋ ታሪፍ ጥለዋል። የአውሮፓ ህብረት የጣለው ታሪፍ ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከውዝግቡ በኋላ፣ ብፕአውሮፓ ህብረት የውስኪ ሽያጭ በ20 በመቶ ቀንሷል።
#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.