በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ክህሎት ያላቸውን ልጆች ማብቃት አላማ ያደረገዉ ማሰልጠኛ ማዕከሉ፤በኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተቋቋመ ነዉ፡፡
ማህበሩ የኮንስትራክሽንና የኢንቴረር ዲዛይን ሥራዎችን በመላ ሀገሪቱ የሚገኙና በሙያው መሰልጠን ለሚፈልጉ ዜጎች ‹‹ሪቪዚት ኢንስቲቱሽን ኦፍ ዲዛይን›› በሚል ማሰልጠኛ ማዕከል ከፍቶ ምዝገባ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡
በዚህ የሥራ መስክ በሀገራችን ብዙ ማሰልጠኛ ተቋማት የሉም የተባለ ሲሆን፤ማህበሩ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በተከተለ መልኩ ስልጠናዎችን እሰጣለሁ ብሏል፡፡
በተጨማሪም በወርክ ሾፖችና የግንባታ ሳይቶች ላይ የተግባር ስልጠናዎችን የሚሰጥ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ማሰልጠኛ ማዕከሉ በኮንስትራክሽን እንዲሁም በአርክቴክቱ ዘርፍ የተማሩ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተናግሯል፡፡
ክፍያቸዉን በፍጥነት መፈጸም ለማይችሉ ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን እስከ 1 ዓመት የሚቆይ የብድር መክፈያ መንገድ እንዳመቻቸም አስታዉቋል፡፡
ስልጠናዎቹ በቀን፣ በማታ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በኦንላይን የሚሰጡ ናቸዉ፡፡
ኤሮ አይረን ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በኢንቴረር ዲዛይንና በኮንስትራክሽን የሥራ መስክ ተሰማርቶ የንድፍ እና የግንባታ ሥራዎች በመሥራት ይታወቃል፡፡



Source: Yeneta Tube









No comments yet.