ዳሞታ ኪኪያ ደብረ ሣህል ቅድስት ሥላሴ ገዳም የወላይታ ህዝብ የክርስትና እና የስልጣኔ መነሻ የሕግና የሥርዓት መፍለቂያ ገዳም መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን??
የወላይታ ታሪክ ስታነሳ ክርስትናን መቼም አትረሳም! ክርስትናን ካነሳክ ደግሞ አቡነ ተክለሃይማኖትን በፍጹም አትረሳም! ፤ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትን ካስታወስክ ደግሞ ታላቅ ተጋድሏቸውን ጣዖታትን ማፈራረሳቸውን ፣ አምልኮተ ጣኦትን አጥፍቶ አምልኮተ እግዚአብሔርን ማጽናታቸውን እና ሀ-ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የማይጠፋውን የወንጌል ችቦን በወላይታ ምድር እንዳቀጣጠሉት ትመሰክራለህ!።
በመቀጠልም በወላይታ ከ50 በላይ ነገስታት መካከል በጦር እና በውጊያ ታዋቂ (An expansionist king of Wolaita or the Golden age of wolaita history) የሆነውን ካዎ ሞቶሎሚን (Sato Motolomi or Motolomi Sato or Kawo Motolomi Sato) ከነ ክርስትና ስማቸው ታውቃቸዋለህ! 👉#ፍስሐ_ጽዮን።
በአምልኮተ ጣኦት አይኑ ታውሮ ልቡ እንደ ድንጋይ ደንድኖ ፡ የክርስቶስ ፍቅር ከልቡ ጠፍቶ ፡ በክርስትያኖች እና በቤተክርስቲያን ላይ ታላቅ መከራ እና ስቃይ ሲያጸናባቸው የነበረው ካዎ (ንጉሥ) ሞቶሎሚ ክርስትና የተነሳው በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን #በዕለተ_ደብረ_ዘይት በዳሞታ ተራራ በኪኪያ ደብረ ሣህል ቅድስት ሥላሴ ገዳም ነበር።
በታላቁ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋ ፱÷፩-፳፯ የክርስትያኖች አሳዳጅ የነበረውን ሳኦልን በደማስቆ መንገድ በድንገት በብርሃን ሰንሰለት ይዞት ሳኦል የነበረውን ስሙን ለውጦ ጳውሎስ ያደረገው መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለማንም የማይገዛውን ኃይለኛውን ሞቶሎሚን በዳሞት ተራራ ላይ በድንገት እነደ ጳውሎስ ይዞት በአባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ላይ አድሮ ሞቶሎሚ የነበረውን ስሙን ለውጦ #ፍስሐ_ጽዮን (የጽዮን ደስታ) ብሎታል።
ሳኦል በክርስቶስ አምኖ ወደ ክርስትና ከተመለሰ በኋላ ክርስቲያኖች እረፍትን እና ነፃነትን እንዳገኙት ሁሉ ካዎ ሞቶሎሚም በክርስቶስ አምኖ ወደ ክርስትና ከተመለሰ በኋላ የወላይታ ክርስትያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ የእረፍ እና የነፃነት አዋጅ በወላይታ ምድር ያወጁበት ጊዜ ነበር።
👉ዳሞታ ኪኪያ ደብረ ሣህል ቅድስት ሥላሴ ገዳም የወላይታ ህዝብ የክርስትና እና የስልጣኔ መነሻ ፡ የህግና የስርዓት መፍለቂያ ገዳም ነው። ሁላችንም ይህን ታላቅ እና ቅዱስ ቦታን ለዓለም የማሳውቅ ግዴታ አለብን።
👉እሁድ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም የተራራውን በዓል የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት #የደብረ_ዘይት በዓልን በዳሞት ተራራ በኪኪያ ደብረ ሣህል ቅድስት ሥላሴ ገዳም እናክብር!።
#ከብፁዕነታቸው_ጋር_እንጓዝ‼️
Eyayou Moliso 🙏🙏
#ShareThisPost



Source: Yeneta Tube









No comments yet.