የትምህርት እመርታ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአሹ ዘ-አራዳ

#Ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ ቅድመ ታሪክ ሊነሱ የሚችሉ ደቡብ አካባቢ የሸፔ: ድሬዳዋ ዙርያ የለገኦዳ እና የመሳሰሉ የዋሻ ላይ ፅሁፎችና ስዕሎች ባለቤት ነች።

ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይበልጥኑ በክርስትና ዕምነት ደግሞ ከመጀመርያ ምዕተ አመታት ጀምሮ እንደተፃፉ የሚነገርላቸው የድነገጋይ ላይ ፅሁፎች በሳብያን በግሪክና የግዕዝ ቋንቋ የተፃፉትንም ባለቤት ነች።

በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስትናን እንዳስፋፉ የሚነገርላቸው 9ኙ ቅዱሳን ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው ሸንበቆ ቀርፀው ያዘጋጁዋቸው መፅሀፍት ሺ ዘመናትን ተሻግረው ዛሬ ላይ በዓለም ድንቋ ድንቅ ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።

በተለያዩ ሁኔታ የተፃፉት ፅሁፎች የትላንትን ገድል ታሪክና ዕውቀትን ለትውልድ በማሻገር አይነተኛ ሚና የተወጡ ሲሆን ለሀገር ዕድገትና ግንባታ ለማህበረሰብ መጎልበት የላቀ ሚና ተጫውተዋል።

በቅርብ ሊባል በሚችል መቶ አመታት ታሪክ ይበልጡኑም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች ወይም አስኳላዎች ተከፍተው ትውልድ ተቀሮጾባቸዋል። በዘመነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ይበልጥ የትምህርት ቤቶች መስፋፋት የተከናወነ ሲሆን በደርግ ዘመነ መንግስት ደግሞ ታላቅ ስራ ተከውናል።

በፕሬዝዳንት ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ይመራ የነበረው የደርግ ዘመነ መንግስት ማህበረሳባችን ካለበት አለመማር ለማላቀቅ ይቻል ዘንድ በዘመቻ መልክ ሁሉም የማህበረሰባችን አካል ይበልጡንም የቤተሰብ ምሶሶ የሆኑት ጎልማሶችን ዘመናዊ እውቀት ማላበስ ትልቅ እመርታ ያመጣል በማለት

ዕውቀት ለሁሉም!

ያልተማረ ይማር የተማረ ያስተምር

መሀይምነት የዕድገት ፀር ነው

ዕውቀት ይስፋፋ

ዕውቀት የዕድገት መሰረት ነው

በሚሉና ሌሎች መፈክሮች አማካኝነት ጎልማሳ አባቶች ከመሸታ ቤት ተቆጥበው እናቶች የቤት ሥራቸውን ትተው ማንም ከቤቱ እንዳይቀር በቁጥጥርና የሚቀሩት ላይ እርምጃ በመውሰድ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ዕውቀት ለሁሉም እንዲዳረስ ሆናል።

ይህን ሁሉ ያነሳሁት ሰሞኑን ወደመርካቶ ሳቀና በመንገድ ተዘርግቶ ሲሸጡ ካገኘኃቸው መጽሀፍት አንዱ ከስር በምሥል ያያዝኩት መሠረተ ትምህርት ሲሆን እንደው ለትውስታ የትምህርትንም እመርታ ትረዱበትይሆናል በሚል ነው።

ዛሬ ላይም በተለያዩ መልኩ የሚገኙ ዕውቀቶች ዋጋ ይኖራቸዋልና ብዙ ይቀረኛል በሚል ለዕውቀት እንፈልግ እላለሁ!

ለአስተያየት
ashucelebrityethiopia@gmail.com
ይጠቀሙ
ሰላም!






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2