የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ መጽሐፍ
#Ethiopia | በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ የተዘጋጀው ” ንባቡና አንድምታ ትርጓሜው” በዕለተ ሰንበት በዕለተ ሆሣዕና በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ዘማርያን፣ የሰንበት ተማሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት ይመረቃል።
በከመ ይቤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ዓይ አፍ፣ ወዓይ ከናፍር፣ ወዓይ ልሳን፣ ዘይትናገር ሕማማቲሁ ለወልድ፣ ልብ ይትከፈል፣ ወሕሊና ይዘበጥ፣ ነፍስ ትርዕድ፣ ወሥጋ ይደክም፣ ሶበ ይትነገር ሕማማቲሁ ለፍቂር” ከመ ይኩን ሊተ ለተዘክሮ ሕማሙ ለክርስቶስ፣ እንዘ እግዚእ ይርድአነ፣ በፍና ትርጓሜ አስተዳለውክዎ “ለ’፣ ወዓዲ ዝንቱ መጽሐፍ በወርኅ ሚያዝያ በ፭ቱ ሠርቀ ዕለት፣ በ፳፻፲ወ፯ቱ ዓመተ ምሕረት በዕለተ እሑድ በበዓለ ሆሣዕና፣ በ፯ቱ ሰዓተ ቀትር፣ እንዘ ግቡዓን አበዊነ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ወአኃዊነ መምህራን፣ አዕሩገ በረከት፣ ወምእመናን በስመ እግዚአብሔር ይትባረክ! ወበእንተዝ እብል በጽናዐ ፍቅር ክርስቶሳዊት፣ ንሕበር በሥምረተ መንፈስ ቅዱስ በዝንቱ ጉባኤ ዐቢይ ወመንፈሳዊ!
እስመ ጸዋዒ አክባሪ ውእቱ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የጌታን ሕማማተ መስቀሉን የሚናገር፦ ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የጌታ ሕማማተ መስቀሉ በተነገረ ጊዜ ልብ በሐዘን ይለያያል፣ ኅሊና በኅዘን ይሰባበራል፣ ነፍስ ትርዳለች ትንቀጠቀጣለች፣ ሥጋም በሐዘን ይደክማል” ብሎ እንደተናገረ የክርስቶስ የሕማሙ መታሰቢያ ይሆንልኝ ዘንድ፣ ጌታ፣ ክርስቶስ በረዳኢት ሳይለየኝ “መልክአ ሕማማቱን” በአንድምታ ትርጓሜ መንገድ አዘጋጅቼዋለሁ፡፡
ዳግመኛም ይህ መጽሐፍ በአራት ኪሎ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ ሚያዝያ 5/2017 ዓ/ም በዕለተ እሑድ በበዓለ ሆሣዕና ከቀኑ 7:00 አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ወንድሞች መምህራን፣ መራቂ ሽማግሌዎች እና ምእመናን በአንድነት ተሰብስበው በእግዚአብሔር ስም ይመረቃል።
ስለዚህ በክርስቶስ ፍቅር ሆኜ በዚህ ታላቅና መንፈሳዊ ጉባኤ አንድ እንሁን እላለሁኝ።
ጠሪ አክባሪ ነውና!
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.