የዓባይ ግድብ ሐይቅን የሚጠብቅ የባሕር ፖሊስ ተደራጀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ጥበቃ የሚያደርግ የ“ባህር ፖሊስ” መደራጀቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በፌዴራል ፖሊስ የሠራዊት ግንባታ ዋና መምሪያ ስር የኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እስከዳር ብርሃን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዓባይ ግድብ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት አንድ ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው።

ይህንን ረጅምና ስፋት ያለውን ሰው ሠራሽ ሀይቅ ለመጠበቅ እና በአካባቢው ሊፈጸሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የፖሊሲ ኃይል ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል። ከዚህ መነሻነትም የ“ባሕር ፖሊስ” መቋቋሙን ገልጸዋል።

የዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የጥበቃ ሥራው የሚከናወነው በፌዴራል ፖሊስ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር እስከዳር፤ ሰው ሠራሽ ሐይቁን ለመጠበቅ የሚያስችል የሎጀስቲክስ አቅምን የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የባሕር ላይ ውንብድናን መከላከል የሚችል ኃይልን ከትጥቅ ጋር የማደራጀት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይ አደረጃጀቱን ወደ ሥራ ለማስገባትም ከኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በትብብር እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

የ“ባሕር ፖሊስ” ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የተደራጀ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ከመንግሥት በሚሰጠው ተልዕኮ መሠረት ሥራውን በብቃት እንደሚወጣ ተናግረዋል።

#GazettePlus
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: