ስለ ዓለም የቁንጅና ውድድር አንዳንድ እውነታዎች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዓለማችን የመጀመሪያው እና ትልቁ የሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር እአአ በ1951 የተዘጋጀው ሲሆን፤ አዘጋጇ ሀገር ዩናይትድ ኪንግደም ነበረች።

• ዓለም አቀፉን የቁንጅና ውድድር ለተከታታይ 38 ዓመታት ያለማቋረጥ በብቸኝነት ያዘጋጀችው ዩናይትድ ኪንግደም ስትሆን፤ ሁሉም ውድድሮች በለንደን ከተማ የተደረጉ ነበሩ።

• በመጀመሪያውን ውድድር ተሳታፊ ከነበሩት 27 አገራት በማሸነፍ ዘውዱን የደፋችው የስዊድኗ የ22 ዓመት ቆንጆ ክርስቲን ማርጋሬታ ነበረች።

• አፍሪካ በግብፅ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በናይጄሪያ ቆነጃጅት 4 ጊዜ የክብር ዘውዱን መጫን ችላለች።

o ከ72 ዓመታቱ የቁንጅና ውድድር የ19 ዓመቷ ግብፃዊት አንቲገን ኮስታንዳ እአአ በ1954 ዘውዱን የጫናት የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ተወካይ ነበረች

o ደቡብ አፍሪካዊቷ የ18 ዓመት ቆንጆ ፔኔሎፕ አን እአአ በ1958 ዘውዱን መጫን የቻለች ሌላኛዋ አፍሪካዊት ነበረች

o ናይጄሪያዊቷ የ19 ዓመት ወጣት አግባኒ ዳርጎ እኤአ 2001 በደቡብ አፍሪካ የተካሄደውን የቁንጅና ውድድር ያሸነፈች ብቸኛዋ ጥቁር አፍሪካዊት ናት

• በውድድሩ የ72 ዓመታት ታሪክ 16 አሸናፊዎች የ18 ዓመት ወጣቶች ሲሆኑ፤ ከ18 ዓመት በታች አሸናፊ አልተመዘገበም።

• በአንፃሩ በእድሜ ትልቋ የዓለማችን ቆንጆ በ2018 ቻይና ላይ በተካሄደው 68ኛው ውድድር ዘውድ የደፋችው የ26 ዓመቷ ሜክሲኳዊት ቬኒሳ ፖንሴዲሎን ናት

• ሕንድ እና ቬኒዙዌላ እያንዳንዳቸው 6 ጊዜ ዘውድ በመጫን ደጋግመው ውድድሩን ያሸነፉ ሀገሮች ሲሆኑ፤ ጃማይካ እና ዩናይትድ ኪንግደም እያንዳንዳቸው 4 ጊዜ በማሸነፍ 2ኛ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ፣ አይስላንድ እና ስዊድን ደግሞ እያንዳንዳቸው 3 ጊዜ በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

• እአአ በ2003 በሀያት አህመድ አማካይነት በዓለም የቁንጅና ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፋ 6ኛ ደረጃን አግኝታ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ በ2025 ደግሞ በሀሴት ደረጀ አማካይነት 2ኛ መውጣት ችላለች።
#EBC






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: