የሁሉ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበር 4ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

- Advertisement -
Sidebar AD

የሁሉ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበር 4ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውንና ሁለተኛ አመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው እለት የማህበሩ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል

በቀን ከ10 ብር ጀምሮ መቆጠብ የሚችል ዜጋ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማህበሩ አባል በመሆን ብድር ማግኘት የሚችልበትን አሰራር የዘረጋው ማህበሩ አባላቱ በየቀኑ መቆጠብ እስከቻሉ ድረስ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ማህበሩ ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር ድረስ ብድር እንደሚሰጥ ተገልጾ የሞባይል አፕሊኬሽን በመጠቀም አባላት የብድር አገልግሎት መጠቀም የሚያስችላቸውን አገልግሎትም ዘርግቷል፡፡

የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የቦርድ ሠብሣቢ መሳፍንት ደበበ የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ920 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት 60 በመቶ የሚኾኑ አባላቱን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ማኅበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአባላቱን ቁጥር ወደ 22 ሺ በላይ ከፍ ማድረግ ችሏል ያሉት ሳብሳቢው የካፒታል መጠኑንም ወደ 1 .65 ቢሊየን ብር በላይ በማሳደግ በርካታ የብድር አማራጮችን ለኅብረተሰቡ እያቀረበ ይገኛልም ነው ያሉት።

በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ ኮሚሽኑ በአሁን ሰአት ሁሉን አቀፍ መሻሻል እያደረገ እንዳለ ገልፀው የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገበው ስኬት ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ኮሚሽነር አክለውም የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበራት ግልፀኝነትና ታማኘነትን ላይ ተመስርተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል

ማህበሩ የዘመናዊ ኮር ባንኪንግ ተጠቃሚም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ይህም ኮርባንኪንግ ከሁሉም ባንኮች ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ እና ሁሉንም የአገራችንን ባንኮች እንደቅርንጫፍ አድርጎ መጠቀም ስላስቻላቸው፣ የማህበሩ አባላት ከየትኛውም ባንክ ገንዘባቸውን ገቢ ወጪ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ሥራዎችን ያከናወነ ነው። በተለይም የፋይናንስ አገልግሎትን በቀላሉ ማግኘት ለማይችሉ ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ የኾነ አገልግሎት በመስጠት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በ2015 ዓ.ም በ126 ሺ ብር ካፒታል በሃዋሳ ከተማ የተመሰረተው ኅብረት ሥራ ማህበሩ ሲመሰረት 114 ወንድ 28 ሴት በድምሩ 142 አባላት የነበሩት ሲሆን ዛሬ ላይ ከ22 ሺ በላይ አባላት እንዳለው ተነግሯል፡፡






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: