የዛሬ 10 ዓመት የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ቁመና አኩሪ ምዕራፍ ይቀዳጃል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለዘመናት የኢትዮጲያን ስም በከፍታ ማስጠራት ያልቻለው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ቢበዛ ከ10 አመታት በኋላ ኢትዮጲያን የሚያኮራበት ጊዜ ይመጣል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን የተናገሩት የመደመር መንግስት በተሰኘ መፅሀፍ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ነው፡፡

ስፖርቱን ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት ከ 100 በላይ ጥቃቅን ሜዳዎችን ገንብተናል ያሉ ሲሆን፤ ይህ ጅማሮ ነገ ላይ አኩሪ የብሄራዊ ቡድንን ለመገንባት የሚረዳ የልምምድ ሂደት ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡

በኢትዮጲያ አንችልም የሚል ትውልድ ተፈጥሯል ያሉም ሲሆን፤ ነገር ግን ኢትዮጲያ በማንኛውም ሁኔታ ትችላለች ችላም አሳይታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የውልሰው


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2