#FastMereja I በአዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ የሚገኘው ዮድ ጃሜ ሆቴል ዛሬ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም 5 አመቱን በደማቅ ስነ ስርዓት አከበረ። በዛሬው እለትም “ኔሚ” የተሰኘውን የባህል አዳራሽ ስራ አስጀምሯል።
የሆቴሉ ባለቤት አቶ በርታ ባበታ እዚህ ለመድረሳቸው ደንበኞችን፣ ሰራተኞችን እና አጋር ድርጅቶችን አመስግነው ቀደም ሲል ዝነኛ የነበረው ኔሚ ክትፎ ቤት ወደ ዮድ ጃሜ ሆቴል መዛወሩን ገልጸዋል።
ዮድ ጃሜ ሆቴል የሬስቶራንት፣ የባር፣ የስፓ፣ ሳውና፣ ሞሮኮ ባዝ፣ የባህላዊ ምግብና መጠጥ፣ ስብሰባ አዳራሾችን የያዘ ሆቴል ነው።
በአሁኑ ወቅት ለ100 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል። ለሆቴሉ የስኬት ጉዞ አስተዋጾ ላደረጉ አካላት የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።
#ቢዝነስ
Source: FastMereja
No comments yet.