🇪🇹
#Ethiopia | “ረቡዕ ዕለት በሀላባና በከምባታ ዞኖች የነበረው ሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ቀጥሎ፣ በዛሬው ዕለት በሀዲያና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ ቤቶችን አስረክበናል፡፡” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
የተገነቡት መንደሮች፦
◻️ ባለሦስት መኝታ መኖሪያ ቤቶች፣
◻️ የማብሰል ባዮጋዝ፣
◻️ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣
◻️ የዶሮና የንብ ማርቢያ እና
◻️ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ናቸው፡፡
“መርሐ – ግብሩ በተመጣጣኝና አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
🏡 በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች መደገም እንዳለበት አሳስበዋል ያለው ስፑትኒክ ነው።
Source: GetuTemesgen
No comments yet.