ትኩረት የሚስብ ዜና፡ የወሎ ነዳጅ እጣ ፈንታ ሊወሰን ነው!ነዳጅ አርግዛ ምጧ የረዘመባት ወሎ፡ አዋላጅ ልታገኝ ትችል ይሆን?ለበ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ትኩረት የሚስብ ዜና፡ 🔥
የወሎ ነዳጅ እጣ ፈንታ ሊወሰን ነው!
ነዳጅ አርግዛ ምጧ የረዘመባት ወሎ፡ አዋላጅ ልታገኝ ትችል ይሆን?
ለበርካታ ዓመታት ሲነገርለትና ሲጠበቅለት የነበረው የደቡብ ወሎ (ለገሂዳና ወረኢሉ) የነዳጅ ሀብት እልባት ለማግኘት ተስፋ የተጣለበት ውሳኔ ሊሰጥ ነው።
ከፌዴራል እስከ ወረዳ ድረስ የተውጣጡ ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት ቡድን ዛሬ ታኅሣሥ 1/2018 ዓ.ም በቦታው ተገኝተዋል።
ይህ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያቀፈው ቡድን የሚከተሉትን አካላት ያካተተ ነበር፡-
1. ከፌዴራል፣ ክልልና ዞን የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት
2. ከወሎ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች
ቡድኑ ለገሂዳና ወረኢሉ ወረዳዎችን በሚያዋስነው መቸላ ወንዝ አካባቢ በአለት ስንጥቅ ወጥቶ የሚታየውን ነዳጅ በዓይኑ ተመልክቷል።
* የናሙና እና መረጃ ስብስብ:
በአለት ላይ ከሚታየው ፈሳሽ ናሙና ወስደዋል፤ እንዲሁም በ2005 ዓ.ም ከፍተኛ ክምችት እንደሚገኝ አመላክቶት የነበረውን ጎራና ት/ቤት አካባቢን በጂፒኤስ መረጃ መዝግበዋል።
* ቡድኑ በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በወረዳ አስተባባሪ አመራሮችና በሀገር ሽማግሌዎች ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፣ ጠቃሚ ማብራሪያዎችንም አግኝቷል።
መንግሥት ለማዕድን ዘርፍ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጹት ባለሙያዎቹ፣ ዛሬ ያዩትን የተፈጥሮ ሀብት ለሀገር ልማት እንዲውል በቅርበት ክትትል እንደሚደረግበት አረጋግጠዋል።
ይህ ጉብኝት ለዘመናት የቆየውን የነዳጅ ጥያቄ
የመጨረሻ ምላሽ የሚያገኝበት መነሻ ይሆን?
Via Legehida Woreda Communication
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: