#Ethiopia | አሊቲማ ሪልስቴት ህዝብ የሚወደውና የሚያከብረው ተወዳጁን አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧል።
አልቲማ ሪል እስቴት ከተመሰረተ ሶስት አመት የሆነው ገና ከጅምሩ በግንባታ ዘርፍ ረጅም አመታትን ያስቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች የመሰረቱት ድርጅት ነው።
አልቲማ ጥራት ፍጥነትና ታማኝነትን መሰረት አድርጎ “ህልምዎን ይኑሩ”በሚል መሪ ቃል የሚታወቅ የሪል እስቴት ኩባንያ ነው፡፡
በባለፉት ሶስት አመታት ሁለት ግንባታዎችን አጠናቆ ያስረከበ ሲሆን አንድ ግንባታው ደግሞ ለመጠናቀቅ 80 በመቶ በላይ የደረሰ እንደሆነ ተገልጿል።
በተለይ አንደኛው ግንባታው በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ፈላጊውን የኑሮ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆን ከ2.7 ሚሊዮን ብር ጀምሮ በማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።
አልቲማ ሪል እስቴት እንደስሙ ከኩነቶች በላይ በመሆን ምንም አይነት እክሎች ቢገጥመው ለደምበኛ በገባው ቃል መሰረት በማስረከብ ቃል ገብቶ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ፎቶ ከበደ መክብብ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.