#Ethiopia | በአውስትራሊያ ከሰሞኑ በተከሰተው ጥቃት የጀግንነት ስራ የሰራው አህመድ ከአውስትራሊያዊያን የፍቅር ስጦታ ተበርክቶለታል።
አህመድ አል አህመድ ራሱን ለአደጋ አጋልጦ በፈጸመው የላቀ የጀግንነት ተግባር የተደሰቱ አውስትራሊያውያን የገንዘብ አሰባሰብ (fundraiser) ከፍተውለት ገንዘብ ሲያሰባስቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
በትላንትናው እለት በጎፈንድ ሚ ያሰባሰቡትን 2.5ሚሊዮን ዶላር ህክምና እየተከታተለበት በሚገኘው ሆስፒታል ተገኝተው አበርክተውለታል።
መላው ዓለምም “ሰብአዊነትና ሕሊና ባለቤት፣ የአውስትራሊያ ጀግና፣ ዓለም አቀፍ ጀግና” በመሳሰሉት የአድናቆት ቃላት እያወደሱት ይገኛሉ።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ደግሞ “እውነተኛ ጀግና” ሲሉ አወድሰውታል።
ራስ ወዳድነት የሌለበት ጀግንነት መፈጸሙንም በመግለጽም አሞካሽተውታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Source: GetuTemesgen









No comments yet.