#Ethiopia | በድንበር ተሻጋሪ የጎሳ ግጭት ወቅት በሶማሊያ ጠመንጃ ይዘው ከወታደሮች ጋር ሲዘምቱ የታዩት ሁለት የሊቨርፑል ነዋሪዎች ወደ እንግሊዝ ሲመለሱ በፖሊስ ሊጠየቁ እንደሚችሉ ተሰምቷል፡፡የብሪታንያ ዜግነት ያላቸው የ31 ዓመቱ አብዲፈታህ ጉላይድ እና የ30 ዓመቱ ኖህ ኢሂኬዌ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ተጉዘዋል።
ሁለቱም ከቶክስትዝ የሊቨርፑል አካባቢ የመጡ ሲሆን ጥንዶች ብሪኪን እና ሬይዘር በሚል ስያሜ ሙዚቃን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ በተጋራዉ ምስል ላይ ግን የወታደራዊ ደንብ ልብስ ታጥቀዉ ይታያሉ፡፡
ወጣቶቹ ከወታደሮቹ ጋር ያላቸው ተሳትፎ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም የለንደን መንግስት ግን “ከእንግሊዝ ወደ ግጭት ዞኖች የሚሄድና ህገወጥ ተግባር የሚፈጽም ሰው ሲመለስ ምርመራ ይደረግበታል” ብሏል።
ጉላይድ በውጥረት እና ከተቀናቃኙ ከኢሳቅ ጎሳ ጋር ሲፋለም ከነበረው የዋርሳንጀሊ ጎሳ ጋር ግንኙነት አለው።በሰሜን ሶማሊያ በሣናጎ ክልል በባድሃን በሚገኝ ሆቴል ውስጥ የታዩት ጉላይድ እና ኢሂኬዌ በተነሳዉ ጉዳይ ላይ ምላሽ አልሰጡም።
ሶማሊያ ከመምጣታቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ከአራት ሰዎች ጋር በመሆን በታይላንድ ፉኬት በአደንዛዥ ዕፅ ጉደይ በቁጥጥር ስር ዉለዉ ነበር፡፡
ካናቢስ ወይም አደንዛዥ እጽን በወቅቱ መጠቀም በታይላንድ ለግል ጥቅም ከሆነ ህጋዊ ነበር ነገር ግን ያለፍቃድ መሸጥ የተከለከለ ነበር።ሰዎቹ በኋላ ላይ ያለምንም ክስ ተለቀዋል፡፡
#bisratFm
Source: GetuTemesgen









No comments yet.