📌የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዘምዘም የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 1ሺህ ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል አለ
#Ethiopia | ትናንት የወጣዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፥ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ባለፈው ሚያዝያ በሱዳን ዳርፉር ግዛት በሚገኘው የዘምዘም ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ ለሦስት ቀናት ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 1ሺህ ንጹሃንን ገድሏል።
ይህ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ላይ የቀረበ ሌላ ተጨማሪ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ ነው፡፡
ድርጅቱ በመጠለያ ጣቢያዉ የተፈጸመውን እና ቢያንስ የ1 ሺህ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ጥቃት በዝርዝር አቅርቧል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በመጠለያ ጣቢያው ላይ ጥቃት የሰነዘረው የሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል-ፋሽርን ለመቆጣጠር በሚያደርገው የከበባ ስልት ነዉ፡፡
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች ያለፍርድ ግድያ ሰለባ እንደሆኑ የተዘገበ ሲሆን ፥ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ጾታዊ ጥቃቶች መፈጸማቸውም በሰነድ ተረጋግጧል።
የዘምዘም መጠለያ ጣቢያ ከሚያዚያዉ ጥቃት በፊት ከ5መቶ ሺህ በላይ ሰዎች የሚኖሩበት በሱዳን ትልቁ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ነበር።
የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ፥ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጥቃቱን ከመፈጸሙ ከወራት በፊት ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች ወደ መጠለያ ጣቢያው እንዳይገቡ አግዶ እንደነበር አስታዉሷል ያለው ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው፡፡
Source: GetuTemesgen









No comments yet.