“ተከበናል” ህውሃት
“አዲስ ከበባ ተጥሏል በተግባር ተከበናል የነዳጅ እጥረትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታት ህዝብ እየጎዳ ነው ብሏል ህውሃት ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ።
ህወሓት “የፌዴራል መንግሥት ላለፉት አሥር ወራት በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት መገደቡ፣ በትራንስፖርት፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል” ሲል ገለፀ፤ ይህም የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ላይ ሥጋት መፍጠሩን ጠቅሷል።
ህወሓት ታኅሣሥ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያስተላልፈውን የበጀት ድጋፍ ማገዱን ገልጿል። ይህም የጤና፣ የትምህርት፣ የውኃ እና የጽዳት አገልግሎቶችን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴዎች እንዲስተጓጎሉ ከማድረጉም በላይ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንዲቀሩ ማድረጉን አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም በትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ሥር ያሉ ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ መታገዱን ኮንኗል። ይህም የድርጅቶቹ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲቆም እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያለ ደመወዝ እንዲቀሩ ማድረጉን ገልጿል።
“የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚገባውን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ከገደበው አሥር ወራት ሊሞላው ተቃርቧል” ያለው ህወሓት “ይህም የሕዝብና የጭነት ትራንስፖርትን፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ለሴቶችና ለሕፃናት የሚሰጡ የድንገተኛ አምቡላንስ አገልግሎቶችን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ሽባ አድርጓል” ሲል ገልጿል።
@Addis_Reporter

No comments yet.