“ፑቲንን አማልዱኝ ” ዘለንስኪ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ፑቲን ጦርነቱን መጨረስ አይፈልጉም ሲሉ ተናገሩ።

ሩሲያን ሊያስቆም የሚችለው ነገር ማዕቀብ መጣል ፣ ንብረቶቿን እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ፣ የምዕራባውያን ተፅኖ እና የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ናቸው ብለዋል ዘለንስኪ ።

ዘለንስኪ ፑቲን በቅርቡ ለጦር ሚኒስትሮቻቸው የተናገሩት በዩክሬን ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ጦርነቱን ያለማቆም ምልክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ፑቲን የሚያሳዩት ምልክት ለእኛ አዲስ አይደለም፣ ከዚህ በፊት እንደተናገርኩት፣ ፑቲን ጦርነቱን መጨረስ አይፈልጉም።

ጦርነቱን እንዲጨርሱ ለማድረግ አጋሮቻችን ወይ ዲፕሎማሲን አሊያም ማዕቀብን እንደ አማራጭ መውሰድ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

የአሜሪካ አሸማጋዮች በግልፅና በምስጢር ፑቲን ጦርነቱን እንደሚጨርሱ ይናገራሉ ፣እኛም የአሜሪካን እቅድ ጥቅማችን ባስጠበቀ መልኩ እንደግፋለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ወደአራተኛ ዓመቱ እየተሻገረ የሚገኘው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ፣ የዓለም መሪዎችን እና ፖለቲከኞችን መፍትሔ ፍለጋ እንዲባዝኑ አድርጓቸዋል።

#NBC


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2