ምድብ 1. ሞሮኮ 🇲🇦, ማሊ 🇲🇱, ዛምቢያ 🇿🇲, ኮሞሮስ 🇰🇲
ሞሮኮ በ 2030 የዓለም ዋንጫን በማዘጋጀት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ሀገር ለመሆን እየተዘጋጀች ነው:: ጥራታቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት እያደረገች ነው:: ከዚያም በላይ ደግሞ ቶፕ ክላስ ቡድን መገንባት:: ለዚያም ነው በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ከ favorite ቡድኖች አንዷ ሆና ግምት የተሰጣት:: ዋና አሰልጣኙ Walid Regragui በቡድኑ አስደናቂ የሚባል ትራክ ሪከርድ አለው:: የሞሮኮ ቡድን በ elite-level ያሉ ተጫዋቾችን የያዘ ስብስብ ነው::
በዚህ ምድብ ሌላኛዋ ሀገር ማሊ ናት:: የማሊ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ Tom Saintfiet , እኚህ ሰው በኢትዮጵያ ብ.ቡድን ነበሩ (July 2011-Oct 2011)
13 የተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖችን የማሰልጠን ልምድ , ከ underdogs ቡድኖች ጋር ኦቨርአቺቭ የማድረግ ስምና ዝና :: የማሊ ቡድን ወጣት ባለተሰጥኦ ተጫዋቾች ያሉት ነው::
ዛምቢያ ከቀድሞው አሰልጣኟ ጋር ተለያይታለች, ከቶርናመንቱ ሁለት ወራት በፊት (የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ Avram Grant) ታድያ ረዳታቸው የነበረው Moses Sichone የዋና አሰልጣኝነት ሚናውን ተረክቧል:: የ 2012 ቻምፒየኖቹ በ2025 በዚህስ ውድድር?
ኮሞሮስ ዝቅተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ሀገራት ናት, በውድድሩ ከሚሳተፉ ሃገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት:: በጣልያናዊው አሰልጣኝ Stefano Cusin ትመራለች::
ምድብ 2. ግብጽ 🇪🇬 , ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦 , አንጎላ 🇦🇴 , ዚምባብዌ 🇿🇼
በአፍሪካ ዋንጫ በጣም ስኬታማዋ ሀገር ግብጽ, 7 ዋንጫዎች:: ይሁን እንጂ በቅርብ ዓመታት የዋንጫ ድርቅ መቷታል ከ 2010 በሗላ ዋንጫ አላሸነፈችም:: ሞሃመድ ሳላህ የመጀመሪያ International title ለማሳካት:: ይህ ቡድን ሌሎችም የሚጠበቁ ተጫዋቾች አሉት ኦማር ማርሙሽ እና ሞስታፋ ሞሃመድ:: በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነትም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ልምድ ያለው ሆሳም ሀሳን በውድድሩ ይጠበቃል::
ደቡብ አፍሪካ ስድስት በአውሮፓ የሚጫወቱ ሁለት ደግሞ በሳውዲ አራቢያ የሚጫወቱ እና ሌሎች ከዚያው ከሀገር ውስጥ የተሰባሰቡ:: ይህ ቡድን በ Hugo Broos ስር በታክቲካል ኢንተለጀንሱ ይታወቃል:: ምርጥ ፐርፎርማንስ እንደሚያሳይ እና ለየትኛውም ቡድን ከባድ ተጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል::
አንጎላ በቅርብ ዓመታት በተከታታይ ኦቨርአቺቨር ሆናለች:: ስብስቧ የወጣት እና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ውህድ ነው:: ፈረንሳዊው አሰልጣኝ Patrice Beaumelle ቡድኑን ረዘም ላለ ጊዜ ይዘውት ከቆዩት Pedro Gonçalves ኅላፊነቱን ተረክበዋል::
ዚምባብዌ ከወር በፊት ነው አዲስ አሰልጣኝ የሾመችው Mario Marinică . የዎልቭሱ አማካይ Marshall Munetsi ከጉዳቱ አገግሞ ይህንን ስብስብ ተቀላቅሏል::
ምድብ 3. ናይጄሪያ 🇳🇬 , ቱኒዚያ 🇹🇳 , ዩጋንዳ(ኡጋንዳ) 🇺🇬 , ታንዛኒያ 🇹🇿
ያለፈው ውድድር የፍጻሜ ተፋላሚ , ለዓለም ዋንጫ ውድድር ማለፍ ያልቻለችው ሀገር ከዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ብዙ ትጠብቃለች, ቁጭትም አለ:: ማጥቃት ላይ ቅንጦት ያለው ቡድን Victor Osimhen እና Lookman በስብስቧ አሉ:: Tolu Arokodare እና Victor Boniface በዚህ ስብስብ ውስጥ አልተካተቱም:: በዚህ ቡድን ፈተናው የሚድፊልዱን ሚዛን መፈለግ ነው:: Eric Chelle አይቮሪ ኮስት ተወልዶ ለማሊ የተጫወተው ይህ ሰው ናይጄሪያን በዋና አሰልጣኝነት ይመራል::
ቱኒዚያ የ Sami Trabelsi ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በ 10 ጨዋታዎች ክሊን ሺት የጠበቀ , ማንም ሊገጥመው የማይፈልገው ግን ደግሞ በማጥቃት ደካማ:: ይህ ቡድን ከፊት መስመር ተጫዋቾች ድጋፍ ይፈልጋል::
ዩጋንዳ (ኡጋንዳ) አሰልጣኝ Paul Put ለተጫዋቾች ጥሪ ያቀረቡት ከሁልም ዓለማት ነው:: ከ USL ቻምፒየንሺፕ አሜሪካ, Thailand, Tanzania, Rwanda, Romania , Czechia እና ከእንግሊዝ 3ተኛ ቲር Burton Albion. ልዩ ልዩ ዓይነት ተጫዋቾችን የያዘውን ስብስብ እንደ ቡድን ፎርም ማድረግ ለአሰልጣኙ ከባድ ስራ::
ታንዛኒያ ካለፉት አራት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ለሶስተኛ ጊዜ ስትሳተፍ ነው:: በሚቀጥለውም ስለመሳተፏ ዋስትና አላት, ከኬንያ እና ዩጋንዳ (ኡጋንዳ) ጋር በጋራ ውድድሩን ስለምታዘጋጅ:: የአዲሱ አሰልጣኝ (አርጀንቲናዊው Miguel Gamondi) ቀዳሚ ዋና ነገር ቡድኑን የጨዋታዎች አሸናፊ ማድረግ ነው:: እኚህ አሰልጣኝ ያለፉትን 25 ዓመታት በአህጉሪቱ አሳልፈዋል, የተለያዩ ክለቦችን በማሰልጠን, ብሔራዊ ቡድን ሲይዙ ግን የመጀመሪያቸው ነው::
ምድብ 4. ሴኔጋል 🇸🇳 , ዲ.ኮንጎ 🇨🇩, ቤኒን 🇧🇯 , ቦትስዋና 🇧🇼
የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ ቻምፒየን ሴኔጋል ለአሰልጣኟ Pape Thaiw የመጀመሪያው ሜጀር ቶርናመንት ነው:: ሴኔጋል ባለፉት 23 competitive ጨዋታዎች አልተሸነፈችም, በጣም ጥሩ ስብስብ አላት::
ዲ.ኮንጎ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የነበራት ደካማ ብቃት በዚህም ውድድር ዝቅተኛ ግምት እንዲሰጣት ያደርጋል:: ቁልፍ የፊት መስመር ተጫዋቿ Yoane Wissa በስብስቡ የለም::
ቤኒን ባለፉት ሁለት ውድድሮች ካለመሳተፍ በሗላ ተመልሳለች, ለአራተኛ ጊዜ በውድድሩ ትካፈላለች: ጀርመናዊው አሰልጣኝ Gernot Rohr በዉድድሩ የቡድኑን የመሸነፍ ታሪክ ወደ አሸናፊነት የመቀየር ዕድል አላቸው::
ቦትስዋና በዚህ ውድድር ዝቅተኛ ግምት የተሰጠው ቡድን የያዘች ሀገር:: ለሁለተኛ ጊዜ በውድድሩ ትሳተፋለች::
ምድብ 5. አልጄሪያ 🇩🇿 , ቡርኪና ፋሶ 🇧🇫, ኢኳቶሪያል ጊኒ 🇬🇶, ሱዳን 🇸🇩
አልጄሪያ በውድድሩ ዋነኛ የዋንጫ ተፎካካሪ ነገር ግን የምድብ ጨዋታዎች ላይ መበርታት , ከምድብ ማለፍ ይቀድማል:: Vladimir Petković ቡድኑን በጥሩ ስኬት ይዘውታል, እውነተኛ ፈተናቸው ግን የሚጀምረው አሁን ነው:: የቡድኑን መከላከል ማጠንከር ከአጥቂ ተጫዋቾች ምርጣቸውን ማውጣት::
ቡርኪና ፋሶ Brama Traoré በብሔራዊ ቡድኑ ዙሪያ ቆይቷል ረዳት አሰልጣኝ እና የታዳጊዎች አሰልጣኝ ሆኖ, አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋና አሰልጣኝነት:: ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች አሉት Bertrand Traoré, Edmond Tapsoba, እና Hervè Koffi ወጣቶቹን Dango Ouattara እና Cyriaque Irié ጨምሮ::
ኢኳቶሪያል ጊኒ ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ሰርፕራይዚንግ ቡድን የፍጻሜ ተፋላሚዎች ከነበሩት ናይጄሪያ እና አይቮሪ ኮስትም በላይ ምድቡን በበላይነት:: አሁንም ጥራት እና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በስብስቧ ይዛለች::
ሱዳን ባለፋት አስር ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ , ከ 1976 ጀምሮ ለአራተኛ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር:: Kwesi Appiah ሱዳን አቅሟን እንድትጠቀም ያስቻለ አሰልጣኝ ነው:: ሱዳን እዚህ ስኬት ላይ የደረሰችው በጦርነት ውስጥ አልፋ ነው እናም በሜዳ ላይ እያንዳንዱ ጨዋታ ከእግር ኳስም በላይ ትርጉም አለው::
ምድብ 6. አይቮሪ ኮስት 🇨🇮 , ካሜሩን 🇨🇲 , ጋቦን 🇬🇦, ሞዛምቢክ 🇲🇿
Defending champion አይቮሪ ኮስት ለሶስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ስታሸንፍ በውድድሩ ታሪክ አስገራሚ ክስተቶች ነበሩ:: በምድብ ጨዋታ ሁለቱን ተሸንፋ, በውድድሩ መሀል የአሰልጣኝ ለውጥ አድርጋ, በጥሎ ማለፍ ውጤቶችን ቀልብሳ ድል በማድረግ:: አሰልጣኙ Emerse Faé ተስፋ አለው በስብስቡ ምርጫ ላይም ቦልድ ውሳኔዎችንም አሳልፏል Nicolas Pépé እና Simon Adingra በመተው ወጣቶቹ Yan Diomande እና Bazoumana Touré ተካተዋል:: ልምድ እና ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች ያሉት ብርቱ የtitle defence ስብስብ::
ካሜሩን የአምስት ጊዜ የዋንጫው ባለክብር አሁን ላይ ግን የእግር ኳስ አመራሯ ችግር ውስጥ የተጠመደ የተወሳሰበ ነው ብጥብጥ, ሁከት ያለበት:: ያልተረጋጋ! ለውድድሩ ሁለት የተለያየ ስብስብ ያላት አንደኛው የእግር ኳስ ማህበሩን እና አዲስ የተቀጠረውን አሰልጣኝ David Pagouን ወክሎ , ሌላኛው ደግሞ በቡድኑ አሰልጣኝነት ውል ካለው ከ Marc Brys ወገን:: የችግሩ ምንጭ የ Brys እና የ FA ፕሬዝዳንቱ Samuel Etò ግጭት ነው::
ጋቦን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አልነበረችም አሁን ተመልሳለች::
ሞዛምቢክ በውድድሩ ላይ ለስድስተኛ ጊዜ ትሳተፋለች , በጨዋታ የመጀመሪያ አሸናፊነት ለማግኘት:: የአሰልጣኙ Chiquinho Conde ስብስብ ያልተቀየረ, አብሮ የቆየ ነው:: የ 42 ዓመቱ Domingues ጨዋታ የሚያደርግ ከሆነ በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ በእድሜ ትልቁ outfield player ይሆናል::
ሰላም ጎሳዬ ለፋስት መረጃ
Source: FastMereja









No comments yet.