#FastMereja : አንጋፋው የሂፕሆፕ ንጉሥ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ)፣ “ከምን ልጀምር” የተሰኘ አዲስ እና አራተኛ የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጭ ሊያደርስ መሆኑን በዛሬዉ እለት ተገልጿል።
ልጅ ሚካኤል “ዛሬ ይሁን ነገ” በተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሂፕሆፕ አብዮት (Revolution) መፍጠሩ ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት ይፋ የሆነው “ከምን ልጀምር” አልበም፤ በሙዚቃ ጥራት እና በይዘት ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
በአልበሙ ላይ በቅንብር ብቃታቸው የተመሰከረላቸው ሁናንተ ሙሉ እና ዲጄ ሚላ የተሳተፉ ሲሆን፣ ዘመናዊውን የሂፕሆፕ ምት ከኢትዮጵያዊ ቅኝት ጋር አዋህደው አቅርበዋል።
አልበሙ በአጠቃላይ 15 የሙዚቃ ትራኮችን የያዘ ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ወራት እንደፈጀም ተገልፆ በግጥም፣ በዜማ እና በድምጽ የተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።
“ከምን ልጀምር” የተሰኘው አዲስ እና አራተኛ የሙዚቃ አልበም የፊታችን ቅዳሜ፣ ጥር 30 ቀን 2018ዓ.ም በሁሉም የዲጂታል አውታሮች ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።



Source: FastMereja








No comments yet.