በቂ በጀት ባለመኖሩ የምግብ ዘይት ምርትን ከ 5 በመቶ በታች ዝቅ ሊያደርገው እንደሚችል ተገለጸ።

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ የሚገኙ የምግብ ዘይት አምራችሀ ፋብሪካዎች ካላቸው የማምረት አቅም ውስጥ 50 በመቶውን ብቻ እየተጠቀሙ መሆኑን እና ዋናው ችግር በቂ ገንዘብ ወይም በጀት አለመኖሩ እንደሆነም የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት አምራቾች ማኅበር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ትልቅሰው ለታ ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ በቂ የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት ባለመኖሩ ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅማቸው ማምረት አልቻሉም ብለዋል። ትልልቅ የሚባሉ ፋብሪካዎች በቀን ውስጥ ብቻ እስከ 20 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ጥሬ ዕቃ ግብዓት እንደሚያስፍልጋቸውም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሰብል ምርት ተሰብስቦ የሚገባበትና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት በገበያው ላይ በበቂ ሁኔታ የሚገኝበት ወቅት ቢሆንም፣ አምራቾች ግብዓቱን በጅምላ ገዝተው ስበመጋዘን ለማድረግ የሚያስችል የገንዘብ አቅም የላቸውም ብለዋል። ይህም ፋብሪካዎቹ በየቀኑ ጥሬ ዕቃ እየገዙ እንዲያመርቱና ምርታቸውም ወጥ በሆነ ምልኩ እንዳይቀርብ ምክንያት ሆኗል ሲሉ አንሰተዋል፡፡

በሙሉ አቅም አለማምረት ለሀገር ትልቅ ኪሳራ ነው ሲሉ አንስተው አቅርቦቱ ቢጨምር የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣ ህብረተሰቡም ጤናማ ዘይት እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ አምራቾች መሸፈን የቻሉት የሀገሪቱን የዘይት ፍላጎት 20 በመቶውን ብቻ እንደሆነም ጠቁመዋል።

አምራቾችንና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር መንግሥት ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመሆን ለአምራቾች በቂ ብድር እንዲመቻች ጠይቀዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ 10 የሚጠጉ አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ዘርፉ እየተቀላቀሉ ቢሆንም፣ ያለው የበጀት ችግር ካልተቀረፈ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

#አሐዱ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2