#Ethiopia | ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከ9 ዓመታት ቆይታ በኋላ “ኢትዮሪካ” የተሰኘ ስድስተኛ አልበሙን በዛሬው ዕለት በይፋ ለቋል።
በደሀ ሀገር ጎጆ
ከደሀ እናት ጋራ መኖር ያሳመማት
የህይወት ስንክሳር
ከጠይም ፊቷ ላይ ውብ ሳቋን የቀማት፡፡
ያቺ ውድ እህቴ
ያ’ፈር ገፊ አባቷን ሰቀቀን ተረድታ
ለወንድም እርዛት
እራፊ ልታለብስ እርሷ እርቃን ቀርታ
በባእዳን መንደር
ከክብሯ ተናንሳ ማንነቷ ረክሶ
ናፍቆት’ና ተስፋ
ያሸበረው ልቧ ካ’ይኗ እንባን አፍሶ
ሰርክ እያሳቀቀ
በማዳም ቤት ኑሮ ጉልበት ቢከዳትም
ህመሟ ጥልቅ ነው
እንዳሻት ብትሆን እኔ አልፈርድባትም፡፡
አዎ ህልሞች አሏት
በደሀ ሀገር አልጋ
ከደሀ ቤተሰብ እንቅልፍ የታለመ
የጎደፈ ክብሯን
ከሀገር ሸራ ላይ ሊፍቅ የቀለመ፡፡
ስለዚህ ያ”ቺ ሴት
ሀገሬ ናት ለኔ
እልፍ ምስጢር ያላት ከችግሯ ማዶ
ለዚህ ነው የሚያመኝ
ህመሟ በሙሉ ከልቤ ተዛምዶ፡፡
ደሞ አምናለሁኝ
ፈጣሪ ደግ ነው አዲስ ቀን ይመጣል
ከልቧ ሰማይ ስር
የጠለቀው ጠሀይ ሊያደምቃት ይወጣል
ስደት ተረት ሆኖ
የሀገሬም ታሪክ አብሯት ይለወጣል፡፡
Source: GetuTemesgen









No comments yet.