ሚስ አፍሪካን ኤሰንስ ዓለም አቀፍ የውበት ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia |​ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ማሂ ኢቨንትስ በመተባበር የሚያዘጋጁት ታሪካዊው “የሚስ አፍሪካን ኤሰንስ ኢንተርናሽናል” የውበት ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑን በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

​በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ቢኒያም ታዬ እንደገለጹት፣ መሰል ዓለም አቀፍ ኩነቶች አዲስ አበባን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ መዳረሻ ለማድረግ ለሚሰራው ሥራ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ውድድሩ የአፍሪካን ባህልና ውበት ከማስተዋወቅ ባለፈ ለከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት የራሱ የሆነ አወንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ገልጸው፣ ኮሚሽኑ ለዝግጅቱ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

​ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ታላቅ ኩነት ላይ ከ12 የአፍሪካ አገራት የተወከሉ ቆንጆዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ የውድድሩ ዋነኛ ዓላማም የአፍሪካን ውበት፣ ባህል እና አንድነት ማክበር እንዲሁም የሴቶችን አቅም ማጎልበት እንደሆነ ተገልጿል።

​የማሂ ኢቨንትስ መስራችና የ2023 “ሚስ ቢውቲ ኦፍ አፍሪካ” አሸናፊ የሆነችው ማህሌት ገብረዮሐንስ በበኩሏ፣ “አንዲትን ሴት ማብቃት አገርን ማብቃት ነው” በሚል መሪ ቃል ውድድሩ ለአፍሪካውያን ሴቶች የሚገባውን ትኩረት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጻለች።

ውድድሩ አዲስ አበባን ለዓለም አቀፍ ኩነቶች ተመራጭ መዳረሻ የማድረግ ግብ ያለው ሲሆን፣ በቆይታውም የተለያዩ ባህላዊና ማህበራዊ ሁነቶች እንደሚከናወኑ ታውቋል።

ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1