ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | ​ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ላለፉት 20 ዓመታት በትምህርት ዘርፍ የነበረውን ጉዞና ያስመዘገባቸውን ውጤቶች አስመልክቶ በአፍሪካ ሕብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት አክብሯል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ገነት ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደ ተወካዮች ፣ የተማሪ ወላጆችና የቀድሞ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

የዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት መስራች የሆኑት አቶ ዘላለም አማረ ትምህርት ቤቱ የተመሰረተበትን 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ “እያንዳንዱ ልጅ የዓለም ብርሃን የመሆን አቅም አለው” በሚል ጽኑ እምነት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ስኬታማ ጉዞ ማድረጉን ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የተማሪዎችን ስነ-ምግባር ለመገንባትና ለማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት በመስጠት በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመስራት ማክበሩን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

ትምህርት ቤቱ በቀጣይም ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለትውልድ በማዳረስና ማህበረሰባዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገልጿል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: