ዛሬ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ የውድድር ዳግመ ትንሳኤ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ

#Ethiopia | አለም የሚያውቀን ውድድርን ስንሳተፍ እንጂ ስናዘጋጅ አይደለም በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እድሜ ምስረታ ከ65 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግራንድ ፕሪ አዲስ 2026 በብሮንዝ ደረጃ ያለውን ውድድር ዛሬ በጥሩ ሁኔታ አስተናግዳለች።

በውድድሩ መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ግራንድ ፕሪ አዲስ 2026 በብሮንዝ ደረጃ ያለውን ውድድር በጥራት ማካሄዷ አስደስቶት የተሻለ ውድድር የማዘጋጀት አቅም አላት ብሎ በማመኑ በ2027 ኢትዮጵያ የወርቅ ደረጃ ያለውን ውድድር እንድታዘጋጅ ተወስኖላታል።

ግራንድ ፕሪ የወርቅ ደረጃ ውድድር ምንድን ነው?

በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ውስጥ “ግራንድ ፕሪ የወርቅ ደረጃ” ተብሎ የሚጠራው ውድድር ከፍተኛ ደረጃ እና ታላቅ ዝግጅት ያለው መሆኑን ይገልጻል። እነዚህ ውድድሮች በዓለም አቀፍ የስፖርት አካላት በተፈቀዱ መሠረት የሚካሄዱ ሲሆን ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው አትሌቶችን ይሰበስባሉ።

የወርቅ ደረጃ ውድድሮች በአዘጋጅታቸው ጥራት፣ በሚሳተፉ አትሌቶች ደረጃ እና በሚሰጡ ሽልማቶች መጠን ይለያያሉ። በእነዚህ ውድድሮች የሚመዘገቡ ውጤቶች ለዓለም ደረጃ ምዝገባ እና ለታላላቅ ውድድሮች መግቢያ አስፈላጊ ይሆናሉ።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የግራንድ ፕሪ የወርቅ ደረጃ ውድድሮች ለአትሌቶች የተሻለ የውድድር ልምድ ለመግኘት እና በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስማቸውን ለማሳወቅ አስፈላጊ ሚና ይጫወታሉ።
በአጠቃላይ፣ ይህ ዓይነቱ ውድድር በስፖርቱ ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ክብር ያለው ሲሆን ለተወዳዳሪዎችም ታላቅ ዕድል የሚፈጥር ነው።

ስለዚህ ይህ ውድድር ለኢትዮጵያ የውድድር ዳግመ ትንሣኤ ነው በዚህም ስራ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና ሙሉ ስራ አስፈፃሚዎች ምስጋና ይገባቸዋል ጥራት ያለው ስታዲየም ሰርተን ከጨረስን 2029 ወይም 2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማዘጋጀት በትክክል ማሰብ እንጀምራለን።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2