የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማርኮን በኤክስ ገጻቸው ላይ በሊባኖስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ አባል የሆነ ፈረንሳዊ ዛሬ ማለዳ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል መገደሉን አስታወቁ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የሰላም ማስጠበቅ ተልዕኮ አባል የሆኑ ሌሎች ሦስት ወታደሮች መጎዳታቸውን እና ከአካባቢው እንዲወጡ መደረጉን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል።
ማርኮን አሁን ባለው መረጃ ለጥቃቱ ተጠያቂው ሄዝቦላህ ነው ብለዋል።
አክለውም የሊባኖስ ባለሥልጣናት ጥቃቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩት ሰዎች በፍጥነት በቁጥጥር ሥር እንዲያውሉ ጠይቀዋል።
የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም በፈረንሳይ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል።
“የዚህን ጥቃት ሁኔታ ለማወቅ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ አፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግ ጥብቅ መመሪያ አውጥቻለሁ” ሲሉ በኤክስ ፈገጻቸው ላይ በለጠፉት መልዕከት ላይ ተናግረዋል።
“ ይህ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት በሊባኖስ እና በሚደግፏት ወዳጅ የዓለም አገራት ጋር ባላት ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ሳልገልጽ ማለፍ አልፈልግም።”
ሳላም ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው አልገለጹም።








No comments yet.