በወልዲያ ሆስፒታል ለአንዲት ወጣት በተደረገ ቀዶ ህክምና 534 የሀሞት ጠጠር ተወገደለዘጠኝ ዓመታት በህመም ስትሰቃይ የኖረችዉ …

- Advertisement -
Sidebar AD
በወልዲያ ሆስፒታል ለአንዲት ወጣት በተደረገ ቀዶ ህክምና 534 የሀሞት ጠጠር ተወገደ
ለዘጠኝ ዓመታት በህመም ስትሰቃይ የኖረችዉ የ36 ዓመት ወጣት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገላት ህክምና በቁጥር 534 የሆነ የሀሞት ጠጠር በቀዶ ህክምና እንደተወገደላት ህክምናውን የመሩት በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ስማቸዉ አስረስ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል ።
ታካሚዋ ለዘጠኝ ዓመታት ምግብ ለመብላት ስትቸገር እንደነበርና በተለይም በበዓላት ወቅት ቅባት ያለዉ ምግብ ህመሟን እንደሚያስታዉሳት ተገልጿል። ለበርካታ አመታት የጨጓራ በሽታ ነዉ ተብላ ስትታከም እንደነበርና ምንም ለዉጥ ሳይኖራት መቆየቷ ተጠቁሟል። አሁን በተደረገላት ህክምና በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኗ ተገልጿል ።
የሀሞት ጠጠር ብዙ ጊዜ ከሆርሞን እና ከመዉለድ ጋር ተያይዞ በሴቶች ላይ የሚከሰት መሆኑን የገለፁት ዶክተር ስማቸዉ ኮሌስትሮል ወይንም በሰዉነት ዉስጥ ቅባት ሲበዛ ፣በተፈጥሮ የቀይ ደም ሴል የአሰራር ችግር መኖር እና ሀሞትን በሚያስተላልፉ ቱቦዎች ላይ ሀሞት ከተከሰተ ጠጠር የመፍጠር ዕድል ይኖረዋል ብለዋል ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: