ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ

- Advertisement -
Sidebar AD

🇪🇹✨

​የሀገር ባለውለታውን የዶ/ር ፍቅሩ ማሩን መታሰቢያ በማድረግ፣ ታዝማ (TAZMA) የውስጥ ደዌና የቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል በወራቤ ከተማ 4ተኛውን ዙር ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ሊያካሂድ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።

​📌 የዘመቻው ዝርዝር መረጃ፦

​ ከሚያዝያ 13 – 17/2018 ዓ.ም

​ቦታ፦
ወራቤ ከተማ

​ባለሙያዎች
ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያውያን የሆኑና ለዓመታት የካበተ ልምድ ያላቸው የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች።

​ታሪካዊ ጉዞ
ይህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ከዚህ ቀደም በጅማ፣ በጅግጅጋ እና በሀዋሳ ከተሞች በስኬት ተከናውኗል።

“ይህ ዘመቻ ላለፉት 15 ዓመታት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የልብ ሕክምናን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማድረስ በነበረን ጉዞ እምነት ለጣለብን ማኅበረሰብ ውለታ የምንመልስበት ነው” ብለዋል የማዕከሉ ተወካይ። ውስብስብ ሕክምናን በሀገር ውስጥ በራስ አቅም መስጠት መቻሉም ትልቅ የሀገር ኩራት ነው።

​📞 ለበለጠ መረጃ፦

☎️ 0954 88 62 25 / 9893

📍 አድራሻ፦ ጎተራ ኮንዶሚኒየም፣ አዲስ አበባ

​ይህንን መረጃ በማጋራት ለሚፈልጉት ወገኖቻችን እናድርስ! 🙏❤️

​#getu #TazmaMedical #HeartSurgeryEthiopia #DrFikruMaru #Warabe #FreeMedicalMission #HealthEthiopia #EthiopianHeroes #ታዝማ #የልብህክምና #ወራቤ #ነፃህክምና #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1