ኢራን “በውጊያ ሜዳ አዲስ ስልት አለኝ” ስትል አስጠነቀቀች የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ከአሜሪካ ጋር ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ ቴ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢራን “በውጊያ ሜዳ አዲስ ስልት አለኝ” ስትል አስጠነቀቀች

የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ከአሜሪካ ጋር ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ ቴህራን “በውጊያ ሜዳ አዲስ ስልት ለማሳየት እየተዘጋጀች ነው” በማለት አስጠንቅቀዋል።
በሁለቱ አካላት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ነገ እንደሚያበቃ ሲጠበቅ፥ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም የተኩስ አቁሙ የመቀጠል እድል ላይኖረው እንደሚችል ገልጸዋል።
አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ያደርጉታል ለተባለው ድርድር የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ዛሬ ወደ ፓኪስታን ይሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአንጻሩ ከኢራን በኩል እስካሁን በድርድሩ የመሳተፍ ውሳኔ ያልተደረሰ ሲሆን፥ ተወካይዋንም አለመላኳ እየተነገረ ነው።
አሜሪካ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን፥ ከትናንት በስቲያ የኢራንን ሰንደቅ አላማ የሚያውለበልብ የጭነት መርከብን ይዛለች።
ይህን ተከትሎም ቴህራን አሜሪካ ተኩስ አቁሙን ጥሳለች በሚል ክስ አቅርባለች።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: