የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዳግም ሊቀሰቀስ ነው?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ተጥሎ የነበረው የሁለት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያበቃ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰጡት መግለጫ “ድርድር ካልተሳካ ወደ ጦርነቱ ለመመለስ ዝግጁ ነን” ብለዋል።

​እንደ ፓኪስታን አቆጣጠር ዛሬ ማክሰኞ 23:50 GMT ላይ ስምምነቱ ያበቃል። ኢራን እስከ አሁን ወደ ድርድር ጠረጴዛው ለመምጣት ይፋዊ ምላሽ አልሰጠችም።

​”ኢራን የተኩስ አቁሙን ደጋግማ ጥላለች” ያሉት ትራምፕ፣ አሜሪካ አሁን ባለችበት ጠንካራ የድርድር አቋም ኢራን ከመደራደር ውጪ ሌላ ምርጫ የላትም ብለዋል።

​አሜሪካ ኢራን የዩራኒየም ክምችቷን አሳልፋ እንድትሰጥና በምትኩ 20 ቢሊዮን ዶላር የታገደ ገንዘቧ እንዲለቀቅላት ያቀረበችውን ሃሳብ ኢራን “የማይታሰብ ነው” በማለት ውድቅ አድርጋዋለች።

​የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም በመዘጋቱ እና የአሜሪካ ባህር ኃይል በወሰደው እርምጃ የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ ወደ 94 ዶላር ከፍ ብሏል።

ቻይና በበኩሏ የአሜሪካን እርምጃ “አደገኛ” ስትል የጠራችው ሲሆን፣ የፓኪስታን መንግስት የተኩስ አቁሙ እንዲራዘም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሆኖም የሁለቱ ሀገራት ዛቻና ፍጥጫ ቀጠናውን ወደ ከፋ መጠነ ሰፊ ጦርነት ሊከተው እንደሚችል ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

​ዓለም ትንፋሿን ውጣ የነገውን ውሳኔ እየጠበቀች ነው!

​#getu #IranWar2026 #Trump #MiddleEastCrisis #StraitOfHormuz #OilPrices #BreakingNews #Diplomacy #WW3Watch #ኢራን #አሜሪካ #ሰበርዜና #ጦርነት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: